አገልግሎቱ የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለተቸገሩ ወገኖች ማዕድ አጋራ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የገና በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 5 ነዋሪ የሆኑ 40 አባወራዎችና እማወራዎች የአገልግሎቱ የግዥ አስተዳደር ዘርፍ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ እና ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ማዕድ አጋርተዋል፡፡
ም/ዋና ዳይሬክተሩ የእንኳን አደረሳችሁ መልእክት ያስተላለፉ ሲሆን፤ አገልግሎቱ መድኃኒት ከማቅረብ አልፎ ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ ተናግረዉ፤ በቀጣይም ከወረዳዉ አስተዳደር ጋር በመተባበር ድጋፍ ለሚያስፈልጋቸዉ የማህበረሰብ ክፍሎች ቀጣይነት እንደሚኖረዉ ጨምረዉ ገልፀዋል፡፡
አገልግሎቱ ሀገር የምታደርግለትን ጥሪ በመቀበል ለጥሪዉ ተመጣጣኝ ምላሽ በመስጠት ማህበረሰቡ ጤናዉ እንዲጠበቅ በማድረግ ተልዕኮዉን ከመወጣት ባሻገር ማህበራዊ ኃላፊነቱን እየተወጣ እንደሚገኝ የወረዳዉ ዋና ስራ አስፈፃሚ አቶ መስፍን ተሰማ ተናግረዉ፤ ከዚህ በፊት 5 ለሚሆኑ አቅመ ደካሞች የቤት እድሳት እንዲሁም ትምህርት ለትዉልድ በሚለዉ መርሃግብር ለመድኃኒያለም ት/ቤት እና ለሌሎችም ት/ቤቶች ችግር ፈች የሆኑ ድጋፎች እንደተደረገላቸዉ አስታዉሰዉ፤ ሁልጊዜም አገልግሎቱ ከጎናቸዉ በመሆኑ ምስጋና አቅርበዋል፡፡
#ማገልገል ክብር ነዉ
ሰላም ይደግ
