ኤጀንሲው ለቲቢ ህሙማን መድኃኒቶችን በአግባቡ እያቀረበ እንደሚገኝ ተገለፀ።

፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨ ፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ እጀንሲ ለቲቢ ህሙማን መድኃኒቶችን በአግባቡ እያቀረበ እንደሚገኝ በቅዱስ ጴጥሮስ ስፔሻላይዝ ሆስፒታል የሜድካል ዋርድ ኬዝ ቲም አስተባባሪ ዶ/ር ሆሳዓና ፀጋየ ገለፁ።
በጠየቅነው አግባብ መድኃኒቶችን እናገኛለን ያሉት አስተባባሪዋ በሆስፒታሉ ለቲቢ ታካሚዎች 50 አልጋዎች ያሉ ሲሆን 46 ህሙማን እንደሚታከሙ አክለው ገልፀዋል።
30 የሚሆኑት ተኝተው ህክምናቸውን አየተከታተሉ ሲሆን ቀሪዎቹ በተመላላሽነተት ይታከማሉ ሲሉ ተናግረዋል ።
የቲቢ መድኃኒትን የተለማመደ በሸታ ከአደገኝቱም ባሻገር ታካሚዎች የተመጣጠነ ምግብ ስለሚያስፈልጋቸው የእጀንሲው ሠራተኞች በመድኃኒት አቅርቦት ከሚሰጡት ግልጋሎት በተጨማሪ ለህሙማን ያበረከቱት ስጦታ ምስጋና ሊቸራቸው ይገባል ብለዋል።
ይህም ኤጀንሲው ማህበራዊ ግልጋሎቱን እየተወጣ እንዳለ ማሳያ ነው በማለት ተናግረዋል።
በሆስፒትሉ የሴ/ጉ/ዳ/ዳይሬክተር የሆኑት ሲስተር ተወዳድ መርሻ እንደገለፁት ለሠራተኛችና ይህን ጉብኝት ላዘጋጀው የኤጀንሲው የሴ/ወ/ዳይሮከቶሬት ትልቅ አክብሮት እንዳላቸው ተናግረው ተቀናጅተው እንደሚሰሩም አብራርተዋል።
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በመላ ሀገሪቱ 40 የሚሆኑ የቲቢ እና ተያያዝ የህክምና ግብአቶችን ያቀርባል።
supply chain of compassion!!!!