ኤጀንሲው ለእናቶች እና ሕፃናት ጤና የሚውሉ የሕክምና መሣሪያዎች ስርጭት አጠናቀቀ፡፡

October 21, 2019ፊውቸርድ ዜና
ኤጀንሲው ፔሸንት ሞኒተር (patient monitor) ፣ ፌታል ሞኒተር (fetal monitor) እና ፌታል ዶኘለር (fetal doppler) የተሠኙ የእናቶችና ሕፃናት የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች በሁሉም ክልል ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት አሠራጭቶ ማጠናቀቁን የሕክምና መሣሪያዎች ስርጭት ኦፊሠር አቶ ጂአ ኡጋ ገለፁ፡፡
የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎቹ ለነፍሠ-ጡር እናቶች ፅንስ ጤና መከታተያነት እንደሚያገለግሉና አንዲት እናት ከፅንሠቷ እስከ ወሊድ ጊዜዋ ድረስ የእሷንም የሕፃኑንም ጤንነት ለመጠበቅ እንደሚረዳት አቶ ጂአ አስረድተዋል፡፡
አክለውም የሕክምና መሣሪያዎቹ የሕፃኑን የልብ ምት ስርዓት እና የአተነፋፈስ ስርዓት ደህንነት ለመከታተል እንደሚጠቅም አቶ ጂአ አብራርተዋል፡፡
አቶ ጂአ የማሽኖቹ ብዛት 3ሺህ 600 የነፍሰጡርና ፅንስ ጤንነት መከታተያ (fetal doppler)፣ 180 የፅንስ ጤንነት (fetal monitor) እና 100 የህሙማን ጤና መከታተያ (patient monitor) መሆኑንና 24.5 ሚሊየን ብር ወጪ እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡