ኤጀንሲው ለደም ልገሣ ኘሮግራም የሚውሉ ግብዓቶች ማሠራጨቱን ገለፀ፡፡

October 29, 2019ፊውቸርድ ዜና
ኤጀንሲው ጥቅምት 15 ቀን 2012 ዓ.ም. “ደም ለግሠን ሕይወት እናድን” ለተሠኘው የደም ልገሣ ዘመቻ ከ121 ሺህ በላይ ባለ 350 ሚ.ሊትር የደም መሠብሠብያ ከረጢት ስርጭት ማካሄዱን የክምችት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ት ፍሬሕይወት ታምሩ ገለፁ፡፡
ባለሙያዋ የደም መሠብሠብያ ከረጢቶቹ ከ600 ሺህ ብር በላይ ዋጋ እንዳላቸው አስታውቀዋል፡፡
ኤጀንሲው በአሁኑ ሠዓት የተሠበሠበውን ደም ከኤች.አይ.ቪ፣ ጉበት እና ጨብጥ በሽታዎች ለመመርመር የሚውል የቴስት ኪት ስርጭት ለማሠራጨት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ዛሬ ባለሙያዋ ከዝግጅት ክፍሉ ጋር ባደረጉት ቆይታ አብራርተዋል፡፡
በፀሎት የማነ