ኤጀንሲው ለጤና ሚንስትር በድጋፍ የተገኘውን ለቲቢ ምርመራ አገልግሎት የሚውል የGenexpert ማሽን ርክክብ ተካሄደ፡፡

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለጤና ሚኒስቴር በድጋፍ የተገኘውን ለቲቢ ምርመራ አገልግሎት የሚውል የGenexpert ማሽን ጳጉሜ 3 ቀን 2013 ዓ. ም የኢፌድሪ ጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ በተገኙበት ርክክቡ ተካሄዷል።የቲቢ በሽታን ለመቀነስ በሚደረገው ከፍተኛ ጥረት ላይ ስልጠናዎችንና የምርመራ ማሽኖችን ድጋፍ እያደረጉ ላሉ ለUSAIDእና ለአሜሪካ መንግስት ዶ/ር ሊያ ምስጋና አቅርበዋል።የቲቢ በሽታን ለመቀነስና ለመቆጣጠር እንደ ሀገር ለበርካታ ዓመታት ሰፊ ስራችን በመሰራ የስዎችን ሞት ለመቀነስ ቢቻልም አሁንም በበሽታው የሚያዙ ሰዎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ሚኒስተሯ ገልጸዋል፡፡በድጋፍ የተገኘው ማሽን 46 ሲሆን 1 ሚሊየን የአሜሪካን ዶላር ወጪ እንዳለው ተገልጿል።ይህ ማሽን ቲቢና መድኃኒት የተላመደ የቲቢ በሽታን ለመመርመርና ለማከም ከአሁን በፊት ሁለት ቀናት ይፈጅ የነበረውን ጊዜ ወደ ሁለት ሰዓት በማሳጠር ፈጣን የህክምና አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል ተብሏል።አሜሪካና ኢትዮጵያ የረጅም ጊዜ ወዳጅነት እንዳላቸው የገለጹት በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደር ጊታ ፖሲ የቲቢ በሽታን ከኢትዮጵያ ለመቀነስ በሚደረገው ርብርብ ላይ የአሜሪካ መንግስት የበኩሉን አስተወፅኦ ማበርከቱን ተናግረዋል። በዕለቱ የኢፌድሪ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሰ ፣በኢትዮጵያ የአሜሪካ አምባሳደርጊታ ፖሲ ፣የUSAID ዳይሬክተር፣ እና የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልጋሎን ጨምሮ ከፍተኛ አመራሮች በተገኙበት ርክክቡ ተካሄዷል።