ኤጀንሲው ለጤና ተቋማት ከዱቤ ሽያጭ 1.3 ቢልየን ብር መሠብሠቡን አስታወቀ፡፡

June 12, 2020ፊውቸርድ ዜና
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በ2012 በጀት ዓመት ለጤና ተቋማት በዱቤ ከሸጠው የሕክምና መሣሪያና መድኃኒቶች ውስጥ ከ1.3 ቢልየን ብር በላይ መሠብሠቡን የእቅድ ክትትልና ግምገማ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ጌታቸው ፀጋ ሠኔ 5 ቀን 2012 ዓ.ም.ገለፁ፡፡
ኤጀንሲው በ2012 በጀት ዓመት 1.9 ቢሊዮን ብር ወጪ ያላቸው መድኃኒቶችንና የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎችን በዱቤ ሽያጭ አካሂዶ ከ1.3 ቢልየን ብር በላይ መሠብሠቡን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
ዳይሬክተሩ አያይዘውም ካለፉት ዓመታት የተዛወረና ያልተሠበሠበ 978 ሚሊዮን ብር ውስጥ 715 ሚሊዮን ብር መሠብሠቡን አብራርተው እንደ አጠቃላይ ኤጀንሲው በብድር ከሠጠው 2.9 ቢሊዮን ብር ውስጥ 2.1 ቢሊዮን ብር በላይ መሠብሠቡንና የብድር አሠባሠብ አፈፃፀም ከባለፈው ዓመት በተመሳሳይ ከነበረው 46.16% ወደ 70.79% ያደገ መሆኑን አስረድተዋል፡፡
በወቅቱ ክፍያቸውን ለፈፀሙ የጤና ተቋማት ዳይሬክተሩ ምስጋና ያቀረቡ ሲሆን ክፍያቸውን ላልፈፀሙ ተቋማት ወቅቱን ጠብቀው ክፍያ እንዲፈፅሙ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል፡፡