ኤጀንሲው ለCovid 19 የሚውሉ ቬንትሌተሮችን አሠራጨ፡፡

May 8, 2020ፊውቸርድ ዜና
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ለCovid 19 ታማሚዎች የሚውሉ 24 መካኒካል ቬንትሌተሮች ስርጭት ማካሄዱን የሕክምና መገልገያ መሣሪያዎች ባለሙያ አቶ ጂአ ኡጋ ለዝግጅት ክፍሉ ሚያዝያ 29 ቀን 2012 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡
መካኒካል ቬንትሌተሮቹ በአዲስ አበባ የሚሊንየም አዳራሽ ለተዘጋጀው የCovid-19 ሕክምና መከታተያ ጊዜያዊ ማዕከል፣ ለኤካ ኮተቤ ሆስፒታል፣ ለድሬዳዋ፣ ለአማራ፣ ለትግራይ፣ ለደቡብ ብሔር ብሔረሠቦች፣ ለቤንሻንጉል ጉምዝ፣ ለጋምቤላ፣ ለሶማሌ እና ለአፋር ክልል የጤና ቢሮዎች ተሠራጭቷል፡፡
ቬንትሌተሮቹ በኤጀንሲው አዳማ ቅርንጫፍ በኩል የተሠራጩ ሲሆን 10 ሚሊየን 839 ሺህ 700 ብር ወጪ እንዳላቸው በቃለ መጠይቁ ያገኘነው መረጃ ያሣያል፡፡