ኤጀንሲው ከ 200 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን 50 የኤክስ ሬይ ማሽኖች ስርጭት እያካሄደ ነው፡፡ ====================================================
በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከ223,137,898.00 ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን ዘመናዊ ድጅታል x_ ray machine በመላ ሃገሪቱ ለሚገኙ ሆስፒታሎች እያሰራጨ እንደሚገኝ በኤጀንሲ የፕ/መ/ህ/መገ/የስርጭት ቡድን መሪ የሆኑት አቶ ሽፈራው በቀለ የካቲት 18/6/12 ዓ.ም ገልጸዋል፡፡
እንደ አቶ ሽፈራው ማብራሪያ ከሆነ ቀደም ሲል በጠቅላላው 50 የሚሆኑ ለትግራይ ክልል 4 ፡ለአፋር ክልል 2፡ለአማራ ክልል 13፡ለኦሮሚያ ክልል 16፡ደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል 10፡ለሶማሌ ክልል 2 ፡ለቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 2 እንዲሁም ለጋንቤላ ክልል 1 የኤክስ ሬይ ማሽኖች ለየሆስፒታሎቹ እንደተሰራጩ እና የመጀመሪያዎቹ ማሽኖች በየሆስፒታሎቹ ተተክለው አገልግሎት መስጠት እንደጀመሩ ተናግረዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ ብዛታቸው 50 የሚሆኑ ተመሳሳይ መለያ መስፈርት/specification /ያላቸው እና የየሆስፒታሎችን ፍላጎት መሰረት በማድረግ ለትግራይ ክልል 4 ፡ለአፋር ክልል 2፡ለአማራ ክልል 9፡ለኦሮሚያ ክልል 16፡ደቡብ ብ/ብ/ህ/ክልል 10፡ለሶማሌ ክልል 4 ፡ለቤኒሻንጉል ጉምዝ ክልል 1፡አዲስ አበባ ከተማ 4፡ እንዲሁም ድሬዳዋ ከተማ አስተዳደር 1 ማሽኖችን አያሠራጨን እንገኛለን ብለዋል፡፡
Supply chain of compassion!!!!!!!
በአወል ሀሰን