ኤጀንሲው ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ያላቸው የቤተሠብ ምጣኔ እንዲሁም የእናቶችና ሕፃናት መድኃኒቶችን አሰራጨ፡፡

May 27, 2020ፊውቸርድ ዜና
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ባለፉት 9 ወራት ከ1.1 ቢሊዮን ብር በላይ ወጪ ያላቸው የቤተሠብ ምጣኔ እንዲሁም የእናቶችና ሕፃናት ግብዓቶችን እንዳሠራጨ የእናቶችና ሕፃናት ጤና አገልግሎት ባለሙያ አቶ አድማሱ ውብአንተ ግንቦት 14 ቀን 2012 ዓ.ም. ገለጹ፡፡
ኤጀንሲው ግብዓቶቹን ባሉት 18 ቅርንጫፎች አማካኝነት በመላው ሃገሪቱ ለሚገኙ የጤና ተቋማት ያሠራጨ ሲሆን ባለፉት 9 ወራት ውስጥ 1 ቢሊዮን 134 ሚሊየን 123 ሺህ 157 በላይ የቤተሠብ ምጣኔ እና የእናቶችና ሕፃናት ግብዓቶችን አሠራጭቷል፡፡
ኤጀንሲው ካሠራጫቸው መካከልም ልዩ ልዩ የቤተሠብ ምጣኔ ግብዓቶች፣ ለነፍሠ ጡር እናቶች የሚውል Iron with folic acid፣ ለሕፃናት ፀረ አንጀት ክትትል Albendazol እንዲሁም የተለያዩ ዓይነት ለእናቶች፣ ሕፃናትና ጨቅላ ሕፃናት አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች ይገኙበታል፡፡