ኤጀንሲው የፀረ-ኤች አይ ቪ መድኃኒቶችን ለ1364 የጤና ተቋማት አሰራጨ
የኢትዮጲያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በ2012 በጀት ዓመት ለ1364 የጤና ተቋማት የፀረ-ኤች አይ ቪ እና ተጓዳኝ በሽታ መድኃኒቶችን ማሰራጨቱን የክምችትና የክትትል ባለሞያ የሆኑት አቶ በረከት ተዘራ ነሐሴ 29-ቀን 2012 ዓ.ም ገለጹ፡፡
ኤጀሲው 2 ቢሊዮን 72 ሚሊዮን 794 ሺህ 122 ብር ወጪ ያላቸው የጸረ ኤች አይ ቪ እና ተጓዳኝ በሽታ መድኃኒቶችን መሰራጨቱን ባለሞያው አብራርተዋል፡፡
ስርጭቱም የጸረ ኤች አይ ቪ ህክምናውን ለሚሰጡ በሁሉም ክልሎች ለሚገኙ 1 ሺህ 364 የጤና ተቋማት በኤጀንሲው ቅርጫፎች አማካኝነት 480ሺህ 556 ሰዎች ማከም የሚያስችል መሆኑን ተገልጾዋል፡፡
ሂሩት ሀይሉ