ኤጀንሲው ፋይዘር (Pfizer) የተሰኘ የኮቪድ-19 #የክትባት መድኃኒት ማስቀመጫ ቅድመ ዝግጅቱን ማጠናቀቁ ተገለጸ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ፋይዘር የተሰኘውን #የኮቪድ-19 የክትባት መድኃኒት ማስቀመጫ ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን የመጋዘን ኃላፊ አቶ አማኑኤል ረጋአ መስከረም 24 ቀን 2014 ዓ.ም አስታወቁ፡፡ኤጀንሲው በአሁኑ ሰዓት የክትባት መድኃኒቱን ለማስቀመጥ የሚያገለግሉ አልትራ ሎው #ማቀዝቀዥያ (ULTRA LOW TEMPERATURE FREEZER) የተባሉ እያንዳንዳቸው 828 ሊትር የሚይዙ ብዛት 12 የሆኑ ማቀዝቀዣ ፍሪጆች የተዘጋጁ መሆናቸውን አቶ አማኑኤል ተናግረዋል፡፡ፍሪጆቹ #ከዩኒሴፍ በድጋፍ የተገኙ ሲሆን የሙቀት መጠናቸው -50 እስከ -80 ዲግሪ ሴንቲግሬድ ማቀዝቀዝ እንደሚችሉ ተገልጿ::ፍሪጆቹ በኤጀንሲው በዋናው መ/ቤት ለመጀመሪያ ጊዜ የገቡ ሲሆን በቅርቡ ወደ ሀገር ውስጥ ለሚገባው የፋይዘር ክትባት መድኃኒት ማስቀመጫነት እንደሚያገለግሉ የመጋዘን ሀላፊው አክለዋል፡፡