ኤጀንሲው 1104.8 ኩዩቢክ ሜትር ይዘት የህክምና ግብአት መያዝ የሚችሉ የቅዝቃዜ ሰንሰለት መጋዘን ገንብቶ አስመረቀ::
የኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በመላ ሀገራችን በዋንኛነት ለህጻናት ክትባት፣ ለእናቶች ከወሊድ በኃላ የሚሰጡ መድኃኒቶች፣ የካንሰር መድኃኒቶች፣ የላቦራቶሪ መመርመሪያ ሪኤጀንቶች እንዲሁም ሌሎች የቅዝቃዜ ሰንሰለት ለሚያሥፈልጋቸው ግብአቶች ለማከማቸት የሚያገለግሉ የቀዝቃዛ ሰንሰለት መጋዘን ገንብቶ በዋናው መ/ቤት ግቢ ዛሬ አርብ 24 ቀን 2012 ዓ.ም አስመርቋል፡፡
የተመረቀው የቀዝቃዛ ሰንሰለት መጋዘን 3 የቀዝቃዛ ክፍሎች/cold rooms/ እያንዳንዳቸው 300ሜ ኩዩብ የመያዝ አቅም ያላቸው እና ከ 2 እስከ 8 ድግሪ ሴንቲግሬድ ቅዝቃዜ ለሚያስፈልጋቸው የህክምና ግብዓቶችን ለማከማቸት የሚቻስችሉ ናቸው፡፡ በተጨማሪም 2 የከፍተኛ ቀዝቃዛ ክፍሎች/ freezer rooms / እያንዳንዳቸው 100ሜ ኩዩብ የመያዝ አቅም ያላቸውና ከ -25 እስከ -15 ድግሪ ሴንቲግሬድ ቅዝቃዜ ለሚያስፈልጋቸው የህክምና ግብዓቶች ለማከማቸት የሚቻስችሉ ሲሆኑ በአጠቃላይ መጋዘኑ 1104.8 ኩዩቢክ ሜትር የመያዝ አቅም አለው፡፡
የቅዝቃዜ ክፍሎቹ ሁለት ክፍሎች ያሏቸው በመሆኑ ብልሽት ቢያጋጥም ወይም የመብራት መቆራረጥ መድሃኒቶቹ ሳይበላሹ ከማቆየታቸውም ባሻገር በከፍተኛ ቴክኖሎጅ የተሰሩ በመሆናቸው ደህንነታቸውን እና ጥራታቸውን ጠብቀው ለህብረተሰቡ እንዲደርሱ ይረዳሉ ፡፡
የቅዝቃዜ ክፍሎቹ ተከላ ከባለፈው ነሃሴ የተጀመረ ሲሆን በምረቃ ስነስርዓቱ በተከላው ለተሳተፉ አባላትም የእውቅና ምስክር ወረቀት በተጨማሪ የገንዘብ ሽልማት እንዲሁም ለአጋር ድርጅቶች የእውቅና ምስክር ወረቀት ተሰጥቷል፡፡