ኤጀንሲው Fuanlia Textile PLC – Ethiopia የተባለ የቻይና ኩባንያ ድጋፍ ያደረገውን ከ400 ሺህ በላይ ፌስ ማስክ ተረከበ

May 27, 2020ፊውቸርድ ዜና
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ Zhejiang Fuanlai Co.Ltd (Fuanlia Textile PLC-Ethiopia) የተባለ የቻይና ኩባንያ ድጋፍ ያደረገውን የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ለመከላከል የሚስችሉ ከ419 ሺህ የአፍ እና የአፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል ሚያዝያ 12 ቀን 2012 ዓ.ም ተረክቦ ወደ መጋዘን አስገባ፡፡
ድጋፍ የተደረደው የፊት መሸፈኛ ጭምብል ከ6 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ ያላቸው ሲሆኑ ለተደረገው ድጋፍ ኤጀንሲው ምስጋና እያቀረበ በቀጣይ የኢትዮጰያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በኢትዬጵያ ህብረተሰብ ኢንስቲትውት በሚቀርበው ጥያቄ መሰረት ስርጭቱ የሚካሄድ ይሆናል፡፡