ኤጀንሲው “PMS” የተባለ ስርዓትን ስራ ላይ ለማዋል ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር ስምምነት ተፈራርሟል =======================

ኤጀንሲው ከኢትዮጵያ አየር መንገድ ጋር “EPSA PMS” የተሠኘ ስርዓትን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ጋልጋሎ እና ከኢትዮጵያ አየር መንገድ አቶ ጌትነት ታደሰ የካቲት 10 ቀን 2013 ዓ.ም የመግባቢያ ስምምነት ተፈራርመዋል።”EPSA PMS” የኤጀንሲውን ግቦች በግልጽ ለማስቀመጥ፣ ሰራተኞችን ለማነቃቃት፣ መሻሻሎችን ለመለካትና ግብረ መልስ መስጠት የሚያስችል የአውቶሜሽን ትግበራ ነው ተብሏል፡፡
“EPSA PMS” የኦንላይን ስርዓትን ሲሆን ኤጀንሲው ያቀደውን የ10 ዓመት የመድኃኒት አቅርቦት ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ በውጤታማነት ለማሳካት የሚያግዝ ስርዓት መሆኑ ተገልጿል፡፡
የ”EPSA PMS” ስርዓት አየር መንገዱ በማዘጋጀት ስራ ላይ ያዋለው ቴክኖሎጂ ሲሆን ኤጀንሲውን በማላመድ ለሰራተኞቹ ግልጽ የስራ ኃላፊነትን ከመስጠቱም ባሻገር የቡድን ስራዎችን እንደሚያበረታታና ቁልፍ እሴቶችን ከያዘው ግብ እና ስትራቴጂ ጋር ለማዋሀድ ይጠቅመዋል ፡፡የኤጀንሲው ሰራተኞችም የመፈጸም አቅማቸውን በማሳደግ ጠቃሚ ግብረ መልሶችን ስለ ቀን ተቀን ስራቸው በማግኘት ከግምታዊ ሆነ ልማዳዊ ውሳኔዎች እንዲርቁ ያደርጋል፡፡
“Epsa PMS “በኤጀንሲው በመተግበሩ በዓመት ከ378 ሺህ የአሜሪካን ዶላር በላይ ማዳን ያሥችላል ተብሏል፡፡በስምምነቱ የ “JSI” ከተባለው ግብረ ሰናይ ድርጅት የ GHSC-PSM እና የኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች የተገኙ ሲሆን JSI ለኘሮጀክቱ የገንዘብ ድጋፍ እንደሚያደርግ ተገልጿል፡፡
አወል ሐሠን