ኤጄንሲዉ የመጀመሪያውን 2.2 ሚልዮን ዶዝ የኮረና ቫይረስ ክትባት መረከቡን ገለፀ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በጤና ሚንስቴር በኩል የመጣውን 2.2 ሚልዮን ዶዝ የኮረና ቫይረስ ክትባት ከኢትዮጵያ አየር መንገድ በመረከብ በዋናው መ/ቤት የቅዝቃዜ መጋዘን ማከማቸቱን በኤጀንሲው የመድኃኒት አና ህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ክምችትና ስርጭት አስተዳደር ዘርፍ ም/ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ተስፋዓለም አድራሮ የካቲት 28 ቀን 2013 ዓ.ም ገለፁ።
በኮቫክስ ዓለም አቀፍ ጥምረት የተገኘው 2 ነጥብ 2 ሚሊየን ዶዝ የኮሮና ቫይረስ ክትባቶችን በፍትሃዊነት ለማሰራጨት እንደሚሠራ ነው የተገለፀው።
የመከማቻ ሁኔታዎቹን በተመለከተ(Storage Condition) ከሌሎች ከትባቶች የማከማቻ ሁኔታ ጋር የሚመሳሰል በመሆኑ ከ 2 እስከ 8 ድግሪ ሴንቲግሬድ ማቀዝቀዣ ክፍል እንደሚቆዩ እና ተገቢዉ ክትትል እንደሚደረግላቸዉ ተናግረዋል።
ኤጀንሲው ለስራው ልዩ ትኩረት በመስጠት ማቀዝቀዥያ የተገጠመላቸው ተሽከርካሪዎችን በመጠቀም ክትባቱን በመላ ሀገሪቱ እንደሚያሰራጭ አክለው ገልፅዋል ።
አወል ሀሰን