ከሰክሳሚቶኒየም (Suxamethonium) የተሰኘው የሠመመን ሰጭ መድሃኒት ውጭ ሌሎቹ ሰመመን ሰጪ መድኃኒቶች በበቂ መጠን መኖራቸውን አገልግሎቱ ገለፀ።

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በመድሃኒት የግዥ መዘርዝሩ ተካተው በመላ ሀገራችን ለሚገኙ ጤና ተቋማት የግብአቶችን ምጠና በማድረግ በግዥ ከሚያቀርባቸው፣ ከሚያከማቻቸው እና ከሚያሰራጫቸው የተመረጡ ከአስራ ሁለት (12) አይነት በላይ ለሰመመን ህክምና ከሚውሉት ግብአቶች ውስጥ ከሰክሳሚቶኒየም (Suxamethonium) በስተቀር በሌሎቹ ላይ እጥረት እንደሌለ የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ግንቦት 7 ቀን 2014 ዓ.ም ገለፁ።በመሆኑም መድሀኒቱን ከሚመረትበት ሀገር በዘላቂነት በማስመጣት እንዲሁም አሁን የተፈጠረውን የአቅርቦት መቆራረጥ ችግር በአስቸኳይ ለመቅረፍ በአየር ትራንስፖርት ከጎረቤት ሀገር ለማስገባት እየተሰራ ሲሆን በዚህ ሳምንት ውስጥ እጥረቱ ለተከሰተባቸው ጤና ተቋማት እንዲሰራጭ እናደርጋለን ብለዋል።1. Bupivicaine-0.5% in 10ml ampoule injection 2. Cistracurium-2mg/ml in 10ml ampoule injection 3. Halothane-inhalation4. Isofluroane-250ml-inhalation 5. Ketamine HCL 50mg/ml in 10ml ampoule injection 6. Lidocaine HCL 2% in 20ml injection 7. Lidocaine HCL + adrenalin (2% + 1:200,000) in 20ml vial injection 8. Pethidine HCL – 50mg/ml in ampoule injection 9. Propofol 10mg /ml in 20ml injection 10. Thiopental sodium 0.5g powder for injection 11. Vecuronium bromide 10mg in vial powder for Injection የተባሉት በበቂ መጠን በክምችት ያሉ ሲሆን እነዚህን መድኃኒቶችን በመላው ሃገሪቱ ባሉ 17 ቅርንጫፎቻችን ላይ የሚገኙ በመሆናቸው እንዲሁም በየ ሁለት ሳምንቱ የክምችት ትንተና ሪፖርት በሚደረገዉ የFILL-IFS reporting system በማቅረብ ማግኘት እንደሚቻል ኃላፊው ገልፀዋል። በተጨማሪም ከየቅርንጫፎቻችን ያለዉን ክምችት ወቅታዊ መረጃ ቀጣይነት ባለው መልኩ የምናቀርብ ይሆናል ።
አወል ሀሰን