ከወዳደቁ የብረታ ብረት ቁርጥራጮች ሽያጭ ከ 300ሽህ ብር በላይ ገቢ ተገኘ፡፡ ============================================
በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አጀንሲ ከባለፈው በጀት አመት እና ከዚያ በፊት በወቅቱ መጋዘን ለመቁረጥ ወይም ለመክፈል ከተራረፉ የወዳደቁ የብረታ ብረት ቁርጥራጮች ሽያጭ ከ 300 ሺህ ብር በላይ ገቢ የተገኘ መሆኑን የጠ/አገ/ን/አስ/ዳይሬክቶሪት አስታወቀ፡፡
ዳይሬክተሩ አቶ ፅጋቡ ገብሩ እንደነገሩን ብክነት ሳይኖር ያለንን ሀብት እንዴት በአግባቡ መጠቀም እንደሚገባን ከካይዘን ፍልስፍና ተጨማሪ አውቀት አግኝተንበታል ብለው ስልጠናውም ለእኛ ዳይሬክቶሪት ጠቃሚነቱ የጎላ ነው ብለዋል፡፡
የሀብት ብክነት እየታየ ያለው ምን አይነት ግብአት መቼ እና ለምን እንጠቀማልን የሚል የጋራ እና የተናበበ እቅድ አለመኖሩ ነው ብለዋል፡፡
በአሁኑ ወቅት የንብረት ገማች እና ሻጭ ኮሚቴዎች ተዋቅረው ጥቅም የሚሰጡ እና የማይሠጡ ንብረቶች በአግባቡ በጥንቃቄ በመለየት የኤጀንሲው ከፍተኛ አመራር ውሳኔ አርፎባቸው ወደ ተጨማሪ የሀብት ምንጭነት የሚቀየሩበትን አሰራር እንከተላለን ብለዋል፡፡
በአጋር አካላት የመጡ ለብዙ ጊዜ የቆዩ የሕትመት ውጤቶች በተክለሀይማኖት መጋዘን በብዛት ቦታ ይዘው እንደሚገኙ ገልጸው ለወረቀት ፋብሪካዎች እንደገና እንዲጠቀሙባቸው /Recycle/ በማድረግ ለሀገር ጥቅም እንዲውሉ እየተሰራ ነው ብለዋል፡፡
እንደ አቶ ጥጋቡ ገለጻ አስር የኤጀንሲው ብልሽት ያለባቸው ተሸከርካሪዎች ተለይተው ስምንቱ በአሁኑ ጊዜ ተጠግነው ወደ ስራ እንደገቡ እና ቀሪዎቹም በሂደት ላይ እንዳሉ አስረድተዋል፡፡
በካምፓኒዎች በኩል ለተበላሹ መኪኖች ጥገና ከፍተኛ ወጭ ይጠይቁናል ለአብነት ለአንድ መኪና ስምንት መቶ ሰላሳ አንድ ሺህ ብር እደተጠየቁ እና ጨረታ በማውጣት በአንድ መቶ አምሳ እንድ ሺህ ብር አስጠግነን ስራ ላይ እንዲውል ተደርጓል ብለዋል፡፡
ሁሉም ስራዎች የመንግስትን የግዥ እና ንብረት አወጋገድ ደንብና መመሪያ ተከትለው እንደሚሰሩ ገልጸው በቀጣይም 28 ብልሽት ያለባቸው ተሸከርካሪዎች ተለይተው ጥገና እንደሚደረግላቸው ተናግረዋል፡፡
አቶ አብዲሳ ድንቄሳ በዳይሬክቶሪቱ የንብረት ክፍል ሀላፊ ሲሆኑ በመጋዘን ውስጥ የጽህፈት መሳሪያዎችንና ጎማዎችን ለይተው እንዳስቀመጡና የመጋዘን ጥበት ችግር እንደሆነባቸው ዳሩ ግን የወሰዱት የካይዘን ፍልስፍና ስልጠና ከችግራቸው ለመውጣት ብዙ እውቀት እዳስገኘላቸው እንዲሁም ለመተግበር ቁርጠኝነታቸውን ገልጸውልናል፡፡
በሌላ በኩል ገነት ፀሀይየ የሪከርድ እና ማህደር ሃላፊ ስትሆን አስር አመት ያልሞላቸውን ፋይሎች አርካይቭ ውስጥ አስገብተን በጥንቃቄ አናስቀምጣለን ነገር ግን ረጅም አመት አስቆጥረው የማይወገዱ እንደ ፕላን፣ ካርታ እና የግል ማህደር የመሳሰሉት ሲቀሩ የማይጠቅሙት በጥንቃቄ ተለይተው በመመሪያው መሰረት ቦታ እንዳይዙ መወገድ አለባቸው ብላለች፡፡
Supply chain of compassion!!!