ከ 91 አይነት የጤና ፕሮግራም መድሀኒቶች ውስጥ 89%ቱ ውስን አቅራቢ እንዳላቸው ጥናቶች አመለከቱ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ከሚያቀርባቸው 91 አይነት የጤና ፕሮግራም መድሀኒቶች ውስጥ 81 የሚሆኑት ወይም 89% ያህሉ ውስን አቅራቢ እንዳላቸው ጥናቶች እንደሚያመለክቱ የኤጀንሲው የመድሀኒት ፣የህክምና መሳሪያወች እና መገልገያወች የግዥ አስተዳደር ዘርፍ ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ መጋቢት 16 ቀን 2013 ዓ.ም ገለፁ። ኤጀንሲው ከኢትዮጵያ የምግብ እና መድኃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ሙያተኞች ጋር በተጠና ጥናት መሠረት መረጃዎችን ከሁለቱም ተቋማት ተሠብስቦ 91 የጤና ፕሮግራሞች የኤች አይቪን ጨምሮ ባለፈት ሶስት አመታት ስንት አቅራቢወች አንደነበራቸው እና አሁን ላይ ስንት አቅራቢ እንዳላቸው ለመለየት ተችሏል።81 አይነት ወይም 89% የጤና የፕሮግራም መድሀኒቶች አራት አና በታች ውስን አቅራቢ ነበራቸው ብለዋል።የአቅራቢ ቁጥር ማነስ በራሱ በመድሃኒት መገኘት ምጣኔ ላይ ትልቅ ተፅዕኖ አለው ያሉት ሀላፊው አንድ አቅራቢ ያለው መድሀኒት ያ አቅራቢ በተለያየ ምክንያት ማቅረብ ካልተሳካለት መድሀኒቱ አይቀርብም ነበር ብለዋል። ይህም ሲሆን በአቀርቦት ሰንሠለቱ ላይ ትልቅ አደጋ ነው ብለዋል።28 አይነት መድሀኒቶች ወይም 32% የሚሆኑት ምንም አይነት በሀገር ውስጥ የተመዘገበ አቅራቢ የላቸውም ነበር ይህም ሲባል ግን መድሀኒቶቹ አይቀርቡም ማለት አንዳልሆነ እና በልዩ ሁኔታ እየተፈቀደ ነው እንጂ ተመዝግበው እንልዳልነበረ ነው አቶ ሰለሞን የተናገሩት።ኤጀንሲው ይህንን ችግር ለመፍታት ከምግብና መድሀኒት ቁጥጥር ባለስልጣን ጋር የስትራቴጂ አጋርነት/resourcing strategy /ስምምነት በማድረግ አቅደን እየሠራን ነው ብለዋል።የሦስት አመት የፍሬም ወርክ ስምምነት ከመድኃኒት አቅራቢወች ጋር ውል በመግባት የመደበኛም ሆነ የጤና ፕሮግራም መድሀኒቶች ሳይቆራረጡ እንድቀርቡ ይደረጋል ብለዋል።ኤጀንሲው ከሚያቀርባቸው በአማካይ የመደበኛ አና የጤና ፕሮግራሞችን ጨምሮ79% ውስን አቅራቢ ያላቸው ሲሆን 21% ግን በቂ አቅራቢ እንዳላቸው ጥናቱ ያሳያል ብለዋል።በ ፌደራሉ የግዥ ኤጀንሲ መመሪያ መሠረት ውስን አቅራቢ የሚባሉት 4 አና በታች አቅራቢ ያላቸውን ሲሆን በቂ አቅራቢ የሚባለው በዝቀተኛው 5 አቅራቢ ያለው እንደሆነ መረዳት ተችሗል።
አወል ሀሰን