ከ1ቢሊየን በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶች ወደ አገልግሎት ተቋሙ መግባታቸው ተገለጸ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከ1ቢሊየን በላይ ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶችን ወደ አገልግሎት ተቋሙ ከውጭ ተገዝተው ካሳለፍነው ወር መጨረሻ ጀምሮ ማስገባቱን የመድኃኒትና የህክምና መገልገያዎች የግዥ ኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክተር የሆኑት አቶ ናሆም ገመቹ ህዳር 17 ቀን 2014 ዓ.ም ገለፁ፡፡ወደ ተቋሙ መጋዘኖች ከገቡት መድኃኒቶች መካከል 1 ቢሚሊየን 77ሚሊየን 555ሺ 528 ብረ ዋጋ ያላቸው የህይወት አድን መድኃኒቶች ፣ 161 ሚሊየን 493 ሺ 906 ብር ዋጋ ያላቸው መሰረታዊ መድኃኒቶች እና 2 ሚሊየን 421ሺ 552 የህክምና መሳሪያዎች መሆናቸውን አቶ ናሆም ተናግረዋል ፡፡ከገቡት መድኃኒቶች መካከል Penta vaccine, Omeprazole, Heparine ,Pfizer vaccine, Janssen covid-19 vaccine, HIV test kit, Syringes, Extraction kit, Clozapime Anastrazole, Azathioprine እና Pcv ( PREVENAR 13 50X2ML GVLISE) ዋናነት ተጠቃሽ ናቸው፡፡ መድኃኒቶቹ የህብረተሰቡን የመድኃኒት ፍላጎት ለማሟላት የሚያግዙ ሲሆን በአጠቃላይ 1ቢሊየን 241 ሚሊየን 470ሺ 987 ብር ወጪ እንደተደረገባቸው ዳይሬክተሩ አብራርተዋል ፡፡
ሂሩት ኃይሉ