ከ2 ሚሊየን በላይ ዋጋ ያለው ለአእምሮ ህሙማን ሕክምና አገልግሎት የሚውል መድኃኒት ተሰራጨ

January 25, 2022Featured News
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከ2 ሚሊየን በላይ ዋጋ ያለው ለአእምሮ ህሙማን ሕክምና አገልግሎት የሚውል መድኃኒት ማሰራጨቱን የመድኃኒት ክምችትና ስርጭት ባለሙያ ወ/ሮ ጤናዬ ተክሉ ጥር 3 ቀን 2014 ዓ.ም አስታወቁ፡፡
የተሰራጨው መድኃኒትም 8 ሺህ 190 እሽግ Chlorpromazine 100 mg እና 2 ሺህ እሽግ Chlorpromazine 25 mg-Tablet ሲሆን በአጠቃላይ 2ሚሊየን 302 ሺህ 730ብር ወጪ እንደተደረገበት ተገልጿል፡፡
ስርጭቱም በኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማካኝነት ለሀዋሳ፣ ለባህርዳር፣ ለነጌሌ ቦረና፣ ለጅማ፣ ለሰመራ፣ ለአዲስ አበባ ቁጥር 1 እና 2 የተካሄደ መሆኑን ወ/ሮ ጤናዬ ገልጸው ይህም መድኃኒት20 ሚሊየን 226 ሺህ 269 ብር ግምት ያላው በክምችት እንደሚገኝም አክለዋል፡፡
ሂሩት ኃይሉ