ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ያላቸው የፖሊዮ ክትባት መድኃኒት ስርጭት መካሄዱ ተገለፀ፡፡

October 29, 2019ፊውቸርድ ዜና
ኤጀንሲው ከ20 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ያላቸው የፖሊዮ ክትባት መድኃኒቶችን በበጀት ዓመቱ ስርጭት ማካሄዱን የክትባት ፕሮግራም መድኃኒት ክትትል ባለሞያ ወ/ት ናዲያ ሲራጅ ገለጹ፡፡
የፖሊዮ በሽታ ፖሊዮ በተባለ ቫይረስ የሚመጣ ተላላፊ በሽታ እንደሆነና ጭንቅላት እና ህብረሠረሠርን በማጥቃት የሠውነት አካልን ፖራላይዝ /ሽባ/ ያደርጋል ሲሉ ባለሙያዋ ተናግረዋል፡፡
የፖሊዮ በሽታን ለመከላከል ሕፃናትን ወቅቱን በጠበቀ መልኩ የፖሊዮ ክትባት ማስከተብ እንደሚገባና ኤጀንሲውም ለመላው የሃገሪቱ ሕፃናት የክትባት መድኃኒቱን እንደሚያስመጣ ባለሙያዋ አብራርተዋል፡፡
እንደ ባለሙያዋ ገለፃ ባለፉት 3 ወራት 378 ሺህ 677 ባለ 1ዐ ዶዝ የክትባት መድኃኒቶችን በመላው ሃገሪቱ ለሚገኙ የጤና ተቋማት ስርጭት ተካሂዷል ብለዋል፡፡
በመጪው ሕዳር ወርም በሃገሪቱ እድሜያቸው ከ5 በታች ለሆኑ ሕፃናት የፖሊዮ ክትባት ዘመቻ እንደሚካሄድ ወ/ት ናድያ ገልፀው ኤጀንሲው በየ3 ወሩ የክትባት መድኃኒቶችን ለጤና ተቋማት በመደበኛነት ስርጭት እንደሚያካሂድ ተናግረዋል፡፡
በፀሎት የማነ