ከ30 አይነት በላይ የሚሆኑ የኮቪድ -19 በሽታን ለመመርመሪያና ለመቆጣጠሪያየሚያገለግሉ የህክምና መሳሪያዎች ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ በተገኘ አነስተኛ ወለድ ተገዝተው ርክክብ ተካሄደ

የኮሪያ መንግስት ከኢትዮጵያ መንግስት ጋር ባደረገው የብድር ስምምነት ከኮሪያ ኤግዚም ባንክ በተገኘ የረጅም ጊዜ እና አነስተኛ ወለድ ብድር የተገዙ ከ30 አይነት በላይ የሚሆኑ የኮቪድ -19 በሽታን ለመመርመርና ለመቆጣጠር የሚያገለግሉ የህክምና መሳሪያዎችን ከኮሪያው ኤግዚም ባንክ በተገኘ አነስተኛ ወለድ ተገዝተው ለጤና ሚኒስትር በኢትዮያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ ርክክቡ መጋቢት 24 ቀን 2013 ዓ.ም ተካሄዷል ።የጤና ሚኒስትር ከተረከባቸው የህክምና መሳሪያዎች መካከል መካኒካልቬንትሌተሮች፣ተንቀሳቃሽ ኤክስሬዎች ፣ICE አልጋዎች፣ የኮቪድ መመርመሪያ ማሽኖችና ሌሎች ግብዓቶች የሚገኙበት ሲሆን 30 ሚሊዮን ዶላር ወጪ እንደተደረገባቸው ተገልጿል።
የሕክምና መሳሪያዎቹ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉትን የህክምና ማዕከላት አቅም ለማስፋፋትና ለመገንባት እንዲሁም የፅኑ ህሙማን ታማሚዎችን ህክምና ተደራሽ ከማድረግና ህይወትን ከማዳን አኳያ ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክቱ ዶ/ር ሊያ ታደሰ ተናግረዋል።የኮሪያ መንግስት በሀገራችን የኮቪድ-19 ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ የተለያዩ የሕክምና መሳሪያዎችን በቀጥታ ድጋፍ ያደርግ እንደነበረ የተገለፀ ሲሆን አሁንም በተገኘው ድጋፍ በርካታ የኮቪድ ታማሚዎችን ለመደገፍ የሚያስችል ቢሆንም በሽታውን ለመቆጣጠር የመከላከል ሥራዎች መጠናከር እንዳለባቸው እና መዘናጋት አንደማይገባ ሚንስትሯ በአፅኖት መልክታቸውን አስተላልፈዋል።
በኢትዮጵያ የደቡብ ኮሪያ አምባሳደር ሚስተር ካንግ ሶኪ ከአሁን በፊት 80 ሚሊዮን ዶላር ያወጡ ከግል አና የሀገራቸው የመንግስት ተቋማት የተለገሱ የኮረና መከላከያወችን መለገሳቸውን አስታውሰው ደቡብ ኮሪያ አና ኢትዮጵያ ከ70 አመት በላይ የዘለቀ ወዳጅነት አንዳላቸው ተናግረዋል።
ወጃጅነት፣የማህበረሰብ አቀፍ የጤና አገልግሎት ለኢኮኖሚ ያለውን ፍይዳ አንድሁም በዚህ የኮረና ወረርሽን ወቅት አለም አቀፋ ትስስር አምባሳደሩ በንግግራቸው ትኩረት ያደረጉባቸው ነጥቦች ነበሩ።በእለቱ የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር ሊያ ታደሠ ኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ጋልጋሎ፣የኮሪያው ኤግዚም ባንክ ሀላፊወች በተገኙበት ርክክቡ ተካሄዷ።
ሂሩት ኃይሉ