ከ8 ሚሊየን በላይ ሕፃናትን ማስከተብ የሚችል የፖሊዮ መድኃኒት ክትባት ተሠራጨ፡፡

ኤጀንሲው እድሜያቸው ከ 0 እስከ 59 ወራት ድረስ ለሚገኙ ሕፃናት የክትባት አገልግሎት የሚውል የፖሊዮ ክትባት /Polio SIA (BOPV) መድኃኒት ማሠራጨቱን የመጋዘን አያያዝ ክምችት አስተዳደር ባለሙያ ወ/ሮ ማስተዋል አበባው አስታወቁየክትባት መድኃኒቱ 8.4 ሚሊየን ህፃናትን መከተብ እንደሚያስችል የተገለፀ ሲሆን ለቤንሻንጉል ጉሙዝ፣ ጋምቤላ፣ አፋር፣ አማራ፣ ሐረሪ፣ ሶማሊ እና ኦሮምያ ክልሎች ተሠራጭቷል፡፡የክትባት መድኃኒቱ በኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማካኝነት እየተካሄደ ሲሆን 40 ሚሊየን 764ሺ 673 ከ 04 ሣንቲም ወጪ ተደርጎበታል፡፡
በፀሎት የማነ