ዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያዊያን መብት (ግሎባል አሊያንስ) በኩል ድጋፍ የተደረጉ 11.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮሮና ቫይረስ በሽታ መከላከያ ግብዓቶች ወደ መጋዘን ገቡ፡፡
በዓለም አቀፍ ትብብር ለኢትዮጵያውያን መብት (Global Alliance for the Right of Ethiopians) ድጋፍ የተደረጉ 11.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት የኮሮና ቫይረስ በሽታ መከላከያ ግብዓቶች ሚያዝያ 12 ቀን 2012 ዓ.ም በኤጀንሲው መጋዘን ገቡ፡፡
እነዚህ የህክምና ግብዓቶች 40,000፣ N95 የፊት መሸፈኛ ጭምበል፣ 10,134 ሰርጅካል የፊት መሸፈኛ ጭምበል፣ 25,000 የፊት መከላከያ ፕላስቲክ (Face Shield)፣ የሙቀት መጠን መለኪያ መሳሪያዎች፣ ጓንቶች፣ የህክምና ባለሙያዎች የሚለብሷቸው ሙሉ መከላከያ ልብሶችና ጋዎኖች እና የመሳሰሉት ይገኙበታል::
እነዚህ ግብዓቶች በድጋፍ አስተባባሪው በኩል ለጤና ሚኒስቴር ድጋፍ የተደረጉ ሲሆን በቀጣይ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በኢትዮጵያ ህብረተሰብ ኢንስቲትዩት በሚቀርበው ጥያቄ መሰረት ስርጭቱ የሚካሄድ ይሆናል፡፡