የሀዋሳ ቅርጫፍ በከይዘን ትግበራ ሞዴል ሆኖ ከሐገሪቱ ለተወጣጡ ተቋማት ተሞክሮውን አቀረበ።

በኢትዮጵያ የመድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የሐዋሳ ቅርንጫፍ ባለፉት 2 ዓመታት በከይዘን ትግበራ ባስመዘገበዉ ዉጤት ሞዴል ተቋም ሆኖ ተሞክሮዉን አቀረበ።የኢትዮጵያ የከይዘን ኢንስቲትዩት የከይዘን ፍልስፍና ትግበራን በመላ ሐገሪቱ ለማስረጽ የተለያዩ እስትራቴጂዎችን በመንደፍ ተግባራዊ እያረገ ይገኛል፡፡ከነዚህም አንዱ በከይዘን ትግበራ ሞዴል የሆኑ ተቋማትን በማፍራትና የትግባራ ተሞክሯቸዉን በማስፋት በሐገሪቱ ምርታማነትን ማሳደግ ነዉ፡፡
በዚሁ መሠረት በከይዘን ዙሪያ የተሰሩ ጥናታዊ ጽሑፎችና የተቋማት ተሞክሮ ቀርበዉ የሚመከርበት የጥናትና ምርምር ኮንፈረንስ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት፣ የፐብሊክ ሰርቪስ ኮሚሽን ፣ የከይዘን ኢንሲቲትዩት ከፍተኛ አመራሮች፣ ከዩኒቨርሲቲዎችና ከተለያዩ የመንግስትና የግል ተቋማት የተወጣጡ የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት በአዳማ ከተማ በመካሄድ ላይ ይገኛል፡፡
የኢትዮጰያ የከይዘን ኢንሲቲትዩት ከይዘንን ከሌሎች የሪፎርም መሳሪያዎች ጋር በማቀናጀት ተቋማችንን ትራንስፎርም ለማድረግ በምናደርገዉ ጥረት ለከይዘን ትግበራዉ ዉጤታማነት ለሠጠን ሁለንተናዊ ድጋፍ እናመሰግናለን ሲሉ ኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የሀዋሳ የቅርጫፍ ስራአስኪያጅ አቶ ዘመን ለገሰ በማህበራዊ ሚድያ የትስስር ገፃቸው ላይ አስታውቀዋል።መጨረሻ ለሌለዉ ቀጣይነት ያለዉ ለዉጥ የበለጠ ተግተን እንሰራለን በማለት አቶ ዘመን መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።