የሀገር ውስጥ አምራቾችን የህክምና ግብዓት አቅርቦትን በጋራ ማሳደግ እንደሚገባ ተገለፀ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የሀገር ዉስጥ መድኃኒት አምራቾች ለማሳደግ በቅርበት እየሰራ ይገኛል ፤ በመሆኑም በጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ እና በአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ የሚመራ የሀገር ዉስጥ መድኃኒት አምራች ተወካዮች በተገኙበት የአቅርቦት ሰንሰለቱ መሰረት ያደረ ውይይት አካሄደ ፡፡
አምራቾች የህክምና ግብዓቶችን ለአገልግሎቱ የሚያስረክቡበትን ጊዜና ሂደት ፣ የኤሌክትሮኒክስ መንግስታዊ ግዥ (EGP) ስርዓቱን ማዘመን ፣ የቀጥታ ጨረታ የወጣባቸው የህክምና ግብዓቶች ሂደት ፣ ለሀገር ዉስጥ አምራቾች ቀልጣፋ የክፍያ ስርአትን መዘርጋት ፣ አምራቾች የተሟላ ሰነዶችን ማዘጋጀት ፣ የሀገር ዉስጥ መድኃኒት አምራቾች ሊያቀርቧቸው የሚችሉትን የግብዓት ዝርዝር ማሻሻል እነዚህና በርካታ ሀሳቦች ተነስተው ጥልቅ ውይይት በማድረግ የጋራ መግባባት ተደርሷል ፡፡
በ2016 ዓ.ም ከተጠናቀቁ ጨረታዎች መካከል አምራቾች ባለፉት ስድስት ወራት ለአገልግሎቱ ምን ያህል የህክምና ግብዓቶች ከማቅረብ እንደቻሉ ያላቸውን አፈፃፀም ፣ በ2017 ዓ.ም የወጣው ጨረታ ያለበትን ሁኔታ የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ በዝርዝር አቅርበው ተገምግሟል ።
በቀጣይ ሶስት ወራት አምራቾች 2016 ዓ.ም በወጣው ጨረታ መሰረት ያላስረከቡትን የህክምና ግብዕቶች ሙሉ በሙሉ ለአገልግሎቱ አስረክበው እንዲያጠናቅቁ ፤ የ2017 ዓ.ም በጀት አመት ጨረታ አስፈላጊውን የገበያ ጥናት በመስራት የሁሉም አቅራቢዎች ሙሉ በሙሉ ውል እንዲገቡ ወ/ሮ ፍሬህይወት አበበ አቅጣጫ ሰጥተዋል ።
የጥሬ እቃ ዓብዕቶች እጥረት ፣ የመስርተ ልማት ችግር እየገጠማቸው ተግዳሮቶችን መሆናቸው አምራቾች አንስተው ፤ አገልግሎቱ ከሀገር ውስጥ አምራቾች ጋር ተቀራርቦ ለመስራት የሚያደርገውን ጥረትና ድጋፍ የሚደነቅ ነው ሲሉ የሀገር ውስጥ አምራቾች ም/ፕሬዘዳንት ዶ/ር ታደሰ ቢረስ ምስጋና አቅርበዋል ።
ማገልገል ክብር ነው !
ማኅሌት አበራ





See insights
Boost a post
All reactions:
7272