የህይወት አድንና የመሰረታዊ መድሃኒቶች አቅርቦት አፈፃፀም 86.2% መድረሱ ተገለጸ::
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የ2012 በጀት አመት የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማውን በአዲስ አበባ እምቢልታ ሆቴል ከየካቲት 8 እና9 /2012 አካሄዷል፡፡
በነበረው ዕቅድ ክንውን ውይይት ወቅት ከተነስት ዋና ዋና አፈጻጸሞች በካከል የተወሰኑት እንደሚከተለው ቀርበው ባሉ ጠንካራ እና ደካማ ጎኖች ላይ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡ አፈጻጸሞቹን ከመድኃኒት ክምችት እና ስርጭት ዘርፍ ስንመለከት
· የህይወት አድንና የመሰረታዊ መድሃኒቶች አቅርቦት አፈፃፀም 86.2% መድረሱ የተገለጸ ሲሆን የስድስት ወራት የበጀት አጠቃቀም 67% አንደሆነ ተገልጻል፡፡
· የግዥ ትዕዛዝ ከያዘበት እስከ ኮንትራት የሚፈረምበት ያለውን ጊዜ ከ97 ቀን ወደ 30 ቀን መቀነስ ታቅዶ አፋጻጸሙ 59 ቀናት ማድረስ ተችሏል፡፡
· መድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ግዥ ወደብ ላይ ከደረሰበት ቀን አንስቶ ወደ ኤጀንሲው መጋዘኖች ገቢ እስከሚደረግ የሚወስደውን ጊዜ ከ25 ቀን በታች ማድረግ ታቅዶ አፈጻጸሙ 26 ቀናት ማድረስ ተችሏል፡፡
· የጭነት ትዕዛዝ መጋዘን ደርሶ እስኪጫን ያለውን አማካይ ጊዜ ወደ 3 ቀን መቀነስ Order Turnaround Time (Warehouse Order Cycle time) ታቅዶ 1.6 ቀን መአማካኝ ማድረስ እንደተቻለ ተገልጻል፡፡
· መድሃኒትቶችና የህክምና መገልገያዎች መጋዘን ከደረሱ አንስቶ ገቢ ተደርገው ዋጋ እስኪወጣለት ድረስ ያለው አማካይ ጊዜ ወደ 4 ቀን መቀነስ (Dock to Stock cycle time) ታቅዶ አፈጻጸሙን በአማካኝ 4.2 ቀናት ማድረስ እንደተቻለ ተነግሮረል፡፡
· መድኃኒቶችንና የህክምና መገልገያዎችን ለማሰራጨት የሚወስደውን አማካይ ጊዜ ወደ 7 ቀን መቀነስ (Average delivery time) ታቅዶ አፈጻጸሙም 7 ቀናት እንደሆነ ነው የተገመገመው፡፡
· የጭነት መኪኖች አቅርቦት 100% ማድረስ ታቅዶ 87% ማድረስ ተችሏል፡፡
· ኤጀንሲው የመድሃኒትና ህክምና መገልገያዎች የክምችት፣ የመጋዘን አያያዝና የስርጭት አስተዳደርን ለማሻሻል በዕቅድ ይዞ በመስራት ላይ ይገኛል፡፡
· የእናቶችና ህፃናት ሞትን ለመቀነስ የሚያስችሉ መድሃኒቶችን ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት በተቀናጀ የመድኃኒት አስተዳደር ስርዓት (IPLS) እንዲካተቱ መደረጉ በጥንካሬ ተገልጻል፡፡
· የክትባት አገልግሎት ተደራሽነትን ለማሳደግ የጤና ተቋማት የቀጥታ ስርጭት እየተሰራ ይገኛል፡፡ በዚህም መሰረት ለ294 ሆስፒታሎችና ለ908 ጤና ጣቢያዎች ለክትባት አገልግሎት የሚውሉ መድኃኒቶች በቀጥታ እየቀረበላቸው ሲሆን ከዚህ ዉስጥ አዲስ አበባ 100%፣ ጅማ 93%፣ አሶሳ 84%፣ መቀሌ 100% ሆኗል፡፡
· እንዲሁም የማህጸን በር ጫፍ ካንሰር መከላከያ ክትባት (HPV Vaccine) ለ1000 ወረዳዎቸ የተሰራጨ ሲሆን የፖሊዮ ዘመቻ ለ352 ወረዳዎች እንዲሰራጭ ተደርጓል፡፡
· በየወሩ የክምችት ትንተና በመስራት ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ አጭር የመጠቀሚያ ጊዜ ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያዎችን ከቅርንጫፍ ወደ ቅርንጫፍ በማዟዟር (Re-distrubtion) የብር 4,481,362.99 ዋጋ ያላቸው መድኃኒቶችና የህክምና መገልገያዎችን የመጠቀሚያ ጊዜያቸው ከማለፉ በፊት ጥቅም ላይ እንዲውሉ ተደርጓል፡፡
· በአሁኑ ወቅት በኤጀንሲው ከሚገኙ የጤና ፕሮግራም ክምችት ውስጥ 10 ዋና ዋና ከፍተኛ ክምችት ያላቸው መድሃኒቶችና የህክምና መገልገያ መሳሪያዎች ከ 2 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው የህክምና ግብአቶች እንዳለ ተገልጻል፡፡
· ኤጀንሲው በግማሽ አመት የመደበኛ በጀትና የጤና ፕሮግራም መድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ከ 11 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ግብአቶች ስርጭት አድርጉዋል፡፡
· የመደበኛ በጀትና የጤና ፕሮግራም መድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ከ 9.6 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸው ግብአቶች ክምችት እንዳለ ተብራርቷል፡፡
· የዋናው መስሪያቤት እና የ17 መጋዘኖች CCTV፣ Door Intrusion፣ Smoke Detection and Protection ተከላ የሲቪል ደረጃውን በጠበቀ መልኩ የማስተካከያ ስራ የተከናወነ ሲሆን ከጅማና ቀብሪድሃር ቅርንጫፎች ውጭ ያሉት ቅርንጫፎችና ዋናው መስሪያ ቤት CCTV and Fire Detection ስራ እንዲጀምሩ ተደርጓል፡፡
· እንዲሁም ለሁሉም ቅርንጫፎች CCTV ኦፕሬተሮችና ለመረጃ ስርዓት ባለሙያዎች ስልጠና እንዲያገኙ የተደረገ ሲሆን ለጋምቤላ ቅርንጫፍ የAir Conditionar ግዥ ለማከናወን የመስፈርት ዝግጅት ተጠናቆ በግዥ ሂደት ላይ ይገኛል፡፡
· የመድሃኒትና የህክምና መገልገያዎች የብክነት መጠን ከ2% በታች ማድረስ ለማድረስ ታቅዶ አፈጻጸሙ 1.05% እንደሆነ ተገልጻል፡፡
· የክምችት ቆጠራ ትክክለኛነት ከ86.8% ወደ 100% ለማድረስ ታቅዶ አፈጻጸሙ 89.76% እንደሆነ ተገልጻል፡፡
በ አወል ሀሰን