የሐዋሳ ቅርንጫፍ የካይዘን ፍልስፍናን በመተግበሩ 65 ሚሊዮን ብር ገቢ ተገኘ፡፡

የሐዋሳ ቅርንጫፍ ካለፈው ዓመት ህዳር ወር መጨረሻ ጀምሮ የካይዘን ፍልስፍናን በአግባቡ በመተግበሩ 65 ሚሊዮን ብር ገቢ ማግኘቱን የቅርንጫፉ ሥራ አስኪያጅ አቶ ዘመን ለገሰ ገለጹ፡፡
ገቢው ሊገኝ የቻለው ጥቅም ላይ ሳይውሉ በመጋዘን ተከማችተው የነበሩ የህክምና መገልገያ መሳሪያዎችን በመለየት ለጤና ተቋማት በማሰራጨቱ፣ ራክ ለነጌሌ ቦረና ቅርንጫፍ እንዲሁም ፓሌት ራኮችን ለአርባ ምንጭ ቅርንጫፍ በማሰራጨቱ የተገኘ ውጤት እንደሆነ አቶ ዘመን ተናግረዋል፡፡
አቶ ዘመን በተለይም የመድኃኒት ፍለጋ ጊዜ ማጠር፣ የሥራ ባህል መለወጥና የሥራ ቦታ ምቹ መሆን የለውጥ መሣሪያዎቹ በመተግበራቸው የተገኙ ጥቅሞች መሆናቸውን ስራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
ስራ አስኪያጁ የልህቀት ማዕከልና የካይዘን ትግበራ የሚናበቡ ስራዎችም ናቸው ሲሉ አክለዋል፡፡
ካይዘን ማጣራት፣ ማደራጀት፣ ማጽዳት፣ ማላመድ እና መዝለቅ የሚባሉ ደረጃዎች ያሉት መሆኑንና በአብዛኞቹ የኤጀንሲው ቅርንጫፎች እየተተገበረ ያለ የለውጥ መሳሪያ እንደሆነለ ማወቅ ተችሏል፡፡
የአዳማ ቅርንጫፍ የልህቀት ማዕከል አስተዳደር እና የዋናው መ/ቤት ድጋፍ ለሥራዎቻው ውጤታማነት ትልቅ ድርሻ እንደነበራቸው ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡
በሌላ በኩል የቅርንጫፉ ሙያተኞችና ክላስተሩ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት አባላትና ለመድኃኒት አቅርቦት ሰንሰለት ባለድርሻ አካላት የገባውን ቃል መተግበሩንም አቶ ዘመን ገልጸዋል፡፡
በተያያዘ ዜናም ቅርንጫፉ በልህቀት ማእከል አተገባበር እንዲሁም በዓመታዊ የመድኃኒት ቆጠራ አፈጻጸም 97% በማግኘት ከቅርንጫፎች 1ኛ ደረጃ በመውጣት እውቅና ማግኘቱን ልብ ይሏል፡፡
እኛም ሀዋሳ ቅርንጫፍን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!!!
Supply chain of compassion!!!