የመሠረታዊ ጤና መድኃኒቶች አቅርቦት 72 ፐርሠንት ደረሰ
የመሠረታዊ መድኃኒት አቅርቦት 72 በመቶ መድረሱን የኢትዮጵያ ጤና መድን ኤጀንሲ ያካሔደው ጥናት እንዳሳየ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር ሚዛን ኪሮስ መጋቢት 18 ቀን 2011 ዓ.ም ገለፁ፡፡
የኢትዮጵያ ጤና መድን ኤጀንሲ ከ1000 በላይ የጤና ተቋማት ጋር ውል አስሮ እየሠራ እንደሚገኝና ጥናቱም 30 በመቶ የሚሆኑት የጤና ተቋማትን ማካተቱን ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
የጥናት ውጤቱም ከዚህ ቀደም ከነበረው ውጤት የተሻለ መሆኑንና ቀሪው 28 ፐርሠንት የመድኃኒት እጥረት በጥናቱ ተለይቶ መውጣቱንና ከኢትዮጵያ መድኃኒት አቅርቦት ኤጀንሲም ጋር በጋራ መወያየታቸውን ዶ/ር ሚዛን ገልፀዋል፡፡
ዳይሬክተሩ የሁሉም ዓላማ አንድ መሆኑንና ለጋራ ዓላማ፣ በጋራ መስራትና የስራ ክፍፍል በመውሠድና ለውጡንም እየገመምን መሔድ አለብን ብለዋል፡፡