የመድኃኒት አቅርቦት ስርአቱ ከሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚክ ሪፎርሙ ጋር በተሻለ መልኩ መጣጣም እንዳለበት ተገለፀ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት የስራ አመራር ቦርድ አባላት የካቲት 8 ቀን 2017ዓ.ም ከተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በ11 አጀንዳዎች ዙሪያ በአገልግሎቱ ዋና መስሪያቤት የተወያዩና ዉሳኔ ያስተላለፉ ሲሆን በዋንኛነትም የመድኃኒት አቅርቦት ስርአቱ ከሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚክ ሪፎርሙ ጋር በተሻለ መልኩ መጣጣም እንዳለበት የጋራ መግባባት ላይ ደርሰዋል።
የገንዘብ ሚኒስቴር ሚኒስትርና የአገልግሎቱ ቦርድ ሰብሳቢ የሆኑት አቶ አህመድ ሺዴ እንዳሉት ተቋማዊ ሪፎርሞች ከሀገራዊ ማክሮ ኢኮኖሚክ ሪፎርም ጋር የተናበቡ መሆን እንዳለባቸዉ ገልፀዉ ፤ አገልግሎቱም ስትራቴጃዊ እቅዶቹን ከሀገራዊ ሪፎርሙ ጋር የተጣጣመ ማድረግ እንዳለበት ገልፀዋል።
በተጨማሪም የሀገር ዉስጥ መድኃኒት አቅራቢዎችም የማምረት አቅማቸዉ እያደገ መምጣቱ ጥሩ ቢሆንም ገበያዉ ላይ ተወዳዳሪ መሆን እንዳለባቸዉ የቦርድ ሰብሳቢዉ ተናግረዋል።
የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ለቦርድ አባላቱ ተቋሙ ያለበትን አሁናዊ ሆኔታ ያስረዱ ሲሆን በዋንኛነትም የተቀናጀ የመረጃ አስተዳደር ስርአት (ERP) ትግበራ ወደ ሁለተኛ ምዕራፍ መሸጋገር መቻሉን (Trench 2 Go live) ፤ ነባሩን የተቋሙን መረጃ ማዕከል ማዘመን አስፈላጊ በመሆኑ ከኢትዮ ቴሌኮም ወደ አገልግሎቱ የመረጃ ሽግግር (Data Migration) እየተደረገ እንደሆነ ፤ ግጭቶች ባሉባቸዉ የሀገሪቱ ክፍሎች ተቋሙ የህክምና ግብአቱን እያሰራጨ የሚገኝ ሲሆን የሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላት ድጋፍ እንዳይለይ ጠይቀዋል።
የሀገር ዉስጥ መድኃኒት አምራቾችን የበለጠ ገበያዉ ላይ ተወዳዳሪ እንዲሆኑ ቦርዱ መፍትሄ አምጪ አቅጣጫ ማስቀመጥ እንዳለበትም ዋና ዳይሬክተሩ ጠይቀዋል ።
በመጨረሻም የ2017ዓ.ም የ6 ወራት አፈፃፀምና የክዋኔ ኦዲት ግኝቶች ፤ የአገልግሎቱ የዉስጥ መተዳደሪያ ደንብ ማሻሻያ ነጥቦችና ሌሎች ተቋማዊ አጀንዳዎች ዙሪያ የቦርድ አባላቱና የተቋሙ ከፍተኛ አመራሮች በመወያየት የዉሳኔ ሀሳቦችን አስተላልፏል።




See insights
Boost a post
All reactions:
9898