የማኅጸን በር ካንሰር ክትባት ተሰራጨ /Human Papilloma Virus Vaccine/

October 17, 2019ፊውቸርድ ዜና
ኤጀንሲው ጥቅምት 10 ቀን 2012 ዓ.ም. ለሚካሄደው የማኅጸን በር ካንሰር ክትባት ዘመቻ ከ179 ሚሊየን 396 ሺ ብር በላይ ወጪ ያላቸው የክትባት መድኃኒቶች ማሰራጨቱን የክትባት ፕሮግራም መድኃኒት ክትትል ባለሞያ ወ/ት ናዲያ ሲራጅ ገለጹ፡፡
እንደ ባለሙያዋ ገለፃ የመድኃኒቶቹ ስርጭት በሁሉም የሀገሪቷ ክልሎች ለ1000 ወረዳዎች መካሄዱንና ከ1 ሚሊየን 350 ሺ በላይ ብዛት እንዳላቸው የዝግጅት ክፍሉ ሠምቷል፡፡
ወ/ት ናዲያ አክለውም የክትባት መድኃኒቶቹ ከ14 ዓመት በላይ ላሉ 1 ሚሊየን 286 ሺ 160 ሴቶች እንደሚሠጥ አብራርተዋል፡፡
የክትባት መድኃኒት ስርጭቱ በሚፈለገው የሙቀት መጠን (ከ2 እስከ 8 ሴንቲ ግሬድ ሆኖ ተሰራጭቷል ሲሉ ወ/ት ናዲያ ተናግረዋል፡፡