የሰሜን ምዕራብ ክላስተር 3.5 ቢሊየን ብር መድኃኒቶችን አሠራጨ፡፡

September 16, 2019ፊውቸርድ ዜና
የሰሜን ምዕራብ ክላስተር በ2011 በጀት ዓመት በ2.8 ቢሊየን ብር የኘሮግራም መድኃኒቶች፣ በመደበኛ መድኃኒት 730.6 ሚሊየን ብር በጥቅሉ የ3.5 ቢሊየን ብር መድኃኒቶች ማሠራጨቱ ተገለፀ፡፡
ክላስተሩ በበጀት ዓመቱ ካሣካቸው መካከል የልህቀት ማዕከል ትግበራ በተጠናከረ መልኩ መካሄዱ፣ ቆጠራ በአጭር ጊዜ ተጠናቆ ወደ ሥራ መገባቱ፣ የኢንሲኔሬተር ግንባታ በባህርዳርና ደሴ ተጠናቆ የሙከራ ሥራ መጀመሩ ጥቂቶቹ እንደሆኑ በሪፖርቱ ተመልክተናል፡፡
ክላስተሩ ደሴ፣ ባህርዳር፣ ጎንደርና አሶሳ ቅርንጫፎችን ያቀፈ መሆኑን የባህርዳር ቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አምሣሉ ጫኔ ተናግረዋል፡፡
በበጀት ዓመቱ የአቅርቦት፣ የመጋዘን ፎርክሊፍት አለመኖርና በወቅታዊ የሰላም ችግር ምክንያት አንዳንድ ቦታዎች ላይ መድኃኒቶችን ለማሠራጨት መቸገራቸውን ሥራ አስኪያጁ ገልፀዋል፡፡
በቀጣይም የመድኃኒትና ህክምና መገልገያዎች አቅርቦትን ለማሻሻል ጤና ጥበቃ ቢሮ በአማራ፣ ቤኒሻንጉል ጉሙዝና አፋር ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት ለሚገኙ የጤና ጣቢያዎች የተመደበውን 100 ሚሊዮን ብር ለመጠቀም አቅርቦት ላይ እንደሚሠሩ ተናግረዋል፡፡
ሌላው የጤና ተቋማት ቅሬታ የሆነው የህክምና መሳሪያዎች አቅርቦትና ተከላ ላይ ትኩረት ሠጥቶ እንደሚሠራ ነሐሴ 29 ቀን 2011 በ3ተኛው የአቅርቦት ሠንሠለት መድረክ ላይ ተናግረዋል፡፡