የሰሜን ክላስተር በበጀት ዓመቱ 84% ቀጥታ የመድኃኒት ስርጭት እንደነበረው አስታወቀ፡፡

3ተኛው የአቅርቦት ሠንሠለት መድረክ ነሐሴ 29 ቀን 2011 ዓ.ም. በጎንደር ከተማ በተካሄደበት ወቅት የሰሜን ክላስተር 84% የቀጥታ መድኃኒት ስርጭት እንደነበረው የመቐለ ሥራ አስኪያጅ አቶ አለማየሁ ገ/ማርያም ገለጹ፡፡
የሰሜን ክላስተር በኤጀንሲው 3 ቅርንጫፎችን መቐለ፣ ሽረ እና ሠመራ ቅርንጫፎችን እንደሚያጠቃልል ሪፖርቱ ያሣያል፡፡
መቐለ ቅርንጫፍ ለ203 ጤና ተቋማት 92%፣ ሽረ ቅርንጫፍ ለ100 ጤና ተቋማት 88% እና ሰመራ ቅርንጫፍ ለ84 ጤና ተቋማት 60% የቀጥታ የመድኃኒት ስርጭት ማከናወኑንና በጥቅሉ እንደ ክላስተር 84% ቀጥታ የመድኃኒት ስርጭት መካሄዱን በመድረኩ ተነግሯል፡፡
ክላስተሩ በበጀት ዓመቱ በጤና ፕሮግራም መድኃኒቶች 118% እና በመደበኛ መድኃኒቶች 108% አፈፃፀም በአጠቃላይ 116% አፈፃፀም እንደነበረው ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡
በመደበኛ መድኃኒት ክላስተሩ 22.7 ሚሊየን ብር ወጪ ያላቸው የክምችት ዝውውር ማድረጉ ተገልጿል፡፡
ክላስተሩ በበጀት ዓመቱ ከዋና መሥሪያ ቤት በሚላከው የክፍፍል ድልድል መሠረት መድኃኒቶችን በወቅቱ ማሰራጨቱን ገልጿል፡፡
በ2011 በጀት ዓመት አንዳንድ ሕይወት አድንና መሠረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦት እጥረት ችግር እንዳጋጠመ አስታውቀዋል፡፡
በቀጣይም የአቅርቦት ክፍተት ያለባቸው ህይወት አድንና መሠረታዊ መድኃኒቶች አቅርቦትን ለማሻሻል፣ የፈጣን ለውጥ አምጪና የልህቀት ማእከል ትግበራን ትኩረት ሠጥተን እንሠራለን ብለዋል፡፡
የሠሜን ክላስተር 100.9% የበጀት አፈፃፀም እንደነበረው ሪፖርቱ ያመለክታል፡፡