የቅርንጫፎች የግማሽ አመት እቅድ ክንውን አፈጻጸማቸው ለውይይት ቀርቦ ተገመገመ፡፡ ==========================

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የ2012 በጀት አመት የግማሽ አመት እቅድ አፈጻጸም ግምገማውን በአዲስ አበባ እምቢልታ ሆቴል ከየካቲት 8 እስከ 9 /2012 ዓ.ም የተካሄደ ስሆን የቅርንጫፎችም የግማሽ አመት እቅድ ክንውን አፈጻጸም ለውይይት ቀርቧል፡፡ ከቀረቡት በትቂቱ
• አዳማ ቅርንጫፍ ከ679 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የመድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ለ370 ጤና ተቋማት ስርጭት ከማድረጉም በላይ ለስራ የሚያስፈልጋቸውን ሶፍት ዌር በማላመድ ስራ ላይ አውለዋል፡፡
• አዲስ አበባ ቁጥር1 ከ 1 ቢሊዮን ብር በላይዋጋ ያላቸውን የመድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ለ 134 ወረዳዎች 134 ጤና ተቋማት የክትባት መድኃኒቶችን ጨምሮ አሰራጭቶል፡፡
• አዲስ አበባ ቁጥር 2 የቀጥታ ስርጭት ወደ 19 ጤና ተቋማት ከፍ ማድረጉም በላይ ከ564 ሚሊዮን ብር በላይዋጋ ያላቸውን የመድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ለ370 ጤና ተቋማት ስርጭት አድርጓል፡፡
• ባህር ዳር ቅርንጫፍ ከ 1 .1 ቢሊዮን ብር በላይዋጋ ያላቸውን የመድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ለ 374 ጤና ተቋማት ማሰራጨት ችሏል፡፡
• ደሴ ቅርንጫፍ ከ674 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የመድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ስርጭት እንደነበረው ተገልጻል፡፡
• ጎንደር ቅርንጫፍ ከ346 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የመድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ስርጭት እንደነበረው ተገልጻል፡፡
• መቀሌ ቅርንጫፍ ከ 318 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የመድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ስርጭት እንደነበረው ተገልጻል፡፡የፈጣን ለዉጥ አምጪ ስልት በመተግበር ከ4 ወደ 16 ሆሰፒታሎች ያደገ መሆኑ ተገልፃል
• ድሬ ዳዋ ቅርንጫፍ ከ 804 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የመድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ለ388 ጤና ቋማት ስርጭት እንደነበረው እንዲሁም በሶማሌ ላንድ ተከስቶ በነበረው የጎርፍ አደጋ ለተጎዱ ስዎች የመድሀኒት እርዳታ ተደርገዋል፡፡
• ሽሬ ቅርንጫፍ ከ 89 ሚሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የመድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ስርጭት እንደነበረው ተገልጻል፡፡
• ሃዋሳ ቅርንጫፍ ከ1 ቢሊዮን ብር በላይ ዋጋ ያላቸውን የመድሃኒቶችና የህክምና መገልገያዎች ስርጭት እንደነበረው ተገልጻል፡፡በተለያዩ የለዉጥ መሳሪያዎች/Bsc, Deliverology, KAIZEN ‚QMS‚COE / ተግባራዊ እየተተገበሩ እዳሉ ተገልጻል፡፡
• በኤጀንሲው የህይወት አድንና የመሰረታዊ መድሃኒቶች አቅርቦት አፈፃፀም 86.2% መድረሱን እና የስድስት ወራት የበጀት አጠቃቀሙም 67% አንደሆነ ተገልጻል፡፡
በአጠቃላይ የዋናው መስሪያ ቤት ልዩ ልዩ ዘርፎች እና የሌሎችም ቅርንጫፎች አፈጻጸሞች ቀርበው ጠንካራ እና መሻሻል ያለባቸው አፈጻጸሞች የተለዩ ሲሆን መልካም ተሞክሮችን ማስፋት የቀጣይ ወራት የትኩረት ነጥቦች ተቀምጠዋል፡፡ Supply chain of compassion!!!!! በ አወል ሀሰን