የባህር ዳር ቅርንጫፍ ኢንሲኔሬተር ግንባታ መጠናቀቁ ተነገረ

July 16, 2019ፊውቸርድ ዜና
በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የባህር ዳር ቅርንጫፍ ኢንሲኔሬተር ሙሉ ለሙሉ የግንባታ እና የተከላ ሥራ ተጠናቆ ምረቃ ብቻ እየተጠበቀ መሆኑ ተነገረ፡፡
ኤንሲኔሬተሩ ከሌሎቹ ቅርንጫፍ ኤንሲኔሬተሮች ጋር ተመሣሣይ መሆናቸውን የቅርንጫፍ ሥራ አስኪያጅ አቶ አምሣሉ ጫኔ ተናግረው በሰዓት 5 መቶ ኪሎ ግራም የማቃጠል አቅም እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
ኢንሲኔሬተሩ መሰረተ ልማት መብራት፣ ውኃ፣ መንገድ ያለመሟላቱን ተናግረው ይህንን ችግር ለመቅረፍ ከከተማው መስተዳድርና ከጤና ቢሮው ጋር ተባብረው እየሰሩ መሆናቸውን አስታውቀዋል፡፡
የኢንሲኔሬተሩን ተከላ እና ግንባታ ለማካሄድ ከ45 እስከ 50 ሚሊየን ብር ወጪ አድርገናል ብለዋል፡፡
ኢንሲኔረተሩን ሥራ ለማካሄድ የኤሌክትሮ ሜካኒካል ሰራተኞች እንዲሁም ጥበቃ እንዲቀጠር ተናግረው ወደ ፊት ሥራ ሲጀምር ከ15 እስከ 20 ሰዎች የሥራ እድል ይፈጥራል ብለዋል፡፡
ከዝግጅት ክፍሉ ጋር ሰኔ 11 ቀን ባደረጉት ቆይታ አቶ አምሣሉ ኢንሲኔሬተሩን ሥራ ለማስጀመር እስከ ሐምሌ ወር መጀመሪያ ይመረቃል ተብሎ እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡
በሀዋሳ፣ በአዳማና በነቀምት የተተከሉት ኢንሲኔሬተሮች የሙከራ ሥራቸውን ያጠናቀቁ ሲሆን የባህርዳር ኢንሲኔሬተር ተከላ ተጠናቆ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ የሙከራ ሥራውን እንደሚጀምር ታውቋል፡፡