የአድማስ ኘሮጀክት ትልቅ ተስፋ የተጣለበት መሆኑ ተገለፀ፡፡

ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዓለም አድራሮ
አድማስ ኘሮጀክት የኤጀንሲውን የሰው ኃይል አቅርቦት ሰንሰለት ይቀይራል ተብሎ ትልቅ ተስፋ እንደተሰጠው የኤጀንሲው ምክትል ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋዓለም አድራሮ ሚያዝያ 10 ቀን 2011 ዓ.ም በተካሄደው ሰርቶ ማሳያ መድረክ ላይ ተናገሩ፡፡
ኃላፊው “ባለፋት ዓመታት በኤጀንሲው ብዙ ኢንቨስትመንት ቢፈስም የመድኃኒት አቅርቦቱ የሚፈለገው ደረጃ ላይ አልደረሠም፤ የተቋሙ እድገትም የተፈለገውን ያህል አይደለም” ሲሉ ለፈውስ ጋዜጣ ተናግረዋል፡፡
የሰው ኃይሉ የአቅርቦት ሰንሰለት ሠራተኛ መሆን እንደሚገባው ተናግረው ኤጀንሲው የሚፈለግበት የመድኃኒት አቅርቦት ደረጃ ላይ እንዲደርስ የሰው ኃይሉ ላይ ሊሠራ እንደሚገባ አቶ ተስፋዓለም ጠቁመዋል፡፡
100 ሚሊየን የኢትዮጵያ ሕዝብን ሕይወት የማዳንና ስቃዩን የማስታገስ ኃላፊነት ኤጀንሲው እንዳለበት ኃላፊው አስታውሰው ተቋማችንም በትክክል ሕዝቡ ጋር እንዲደርስ ፕሮጀክቱ ያግዘናል ብለዋል፡፡
ከጽዳት ሠራተኛ እስከ ዋና ዳይሬክተር የአቅርቦት ሠንሠለቱ ሠራተኛ መሆኑንና በእያንዳንዱ እርምጃ የሰውን ህይወት የሚታደግ መሆን እንዳለበት ገልፀው አድማስ ፕሮጀክት የሠራተኛውን የሥራ ባህል በመቀየር ስልጡን የአቅርቦት ሰንሰለት በመፍጠር አስተዋጾ ያበረክታል ብለዋል፡፡
ኘሮጀክቱ ለሠራተኛው ተመሣሣይ አመለካከት ለመፍጠር እና የአቅም ግንባታ ሥራዎችን በመሥራት ያሉብንን ክፍተቶች ይሸፍናል ተብሎ እንደሚጠበቅ አቶ ተስፋዓለም ተናግረዋል፡፡
እንደ ዳይሬክተሩ ገለፃ እንደ ሀገር ሠራተኛው ጥሩ ተከፋይ አለመሆኑና ሁሉም ሠራተኛ ከደመወዝ ባሻገር የያዝነውን ዓላማ ሊያስብ እንደሚገባ ተናግረው የሠራተኛውንም የደመወዝ ጥያቄ የኤጀንሲው ዐዋጅ ሲፀድቅ ምላሽ እንደሚያገኝ ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
የሠራተኛውም የደመወዝ ጥያቄ እስኪመለስ ሠራተኛው የተሠጠውን ኃላፊነትንና ዓላማውን እያሠበ ሕዝቡን በቅንነት እንዲያገለግልና የሕዝቡን ስቃይ እንዲያስታግስ ጥሪ አቅርበዋል፡፡ ����B�{�-