የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ከClinton Health Access lnitiative(CHAI) ልዑካን ቡድን ጋር ተወያዩ

February 18, 2025Magazine
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ከአጋር አካል ድርጅቱ Clinton Health Access lnitiative(CHAI) ልዑካን ቡድን ጋር ድጋፍ በሚያስፈልጉ ጉዳዮች ዙሪያ ሰፊ ዉይይት አድርገዋል።
በዉይይቱ የአገልግሎቱ አሁናዊ የአቅርቦት ሰንሰለት ምን እንደሚመስል ፣ እየተተገበሩ ያሉ የዲጂታል አሰራሮች እንዲሁም ስትራቴጅክ እቅድ ዶ/ር አብዱልቃድር በዝርዝር አቅርበው ፤ በተለይም የክትባቶች ቀጥታ ስርጭትን ለማሳደግ ፣ የቀዝቃዛ ሰንሰለት መጋዘኖች (Cold room) ጥገና እና የመረጃ ግልፀኝነት ላይ ( data visibility ) ሙያዊ ድጋፍ ከአጋር አካሉ እንደሚፈልጉ አፅኖት ሰጥተው ተናግረዋል።
የCHAI በኢትዮጵያ ዳይሬክተር ዶ/ር ራሄል በለጠ እንዳሉት ድጋፎች የበለጠ ተጠናክረው እንደሚቀጥሉና ሌሎች በጋራ ሊሰሩ የሚቺሉ ጉዳዮች ላይ የተሻለ ሙያዊ ድጋፍ እናደርጋለን ሲሉ አንስተዋል።
በዉይይቱ ማጠቃለያ ልዑካን ቡድኑ መጋዘኖችን ተዘዋውረው ተመልክተዋል።
#ማገልገል ክብር ነው!
ሰላም ይደግ





See insights
Boost a post
All reactions:
101101