የአገልግሎቱ የመካከለኛ ዘመን የቀጣይ ሶስት ዓመታት የፋርማሲቲካል እቅድ(PSDIP) ዝግጅት እየተደረገ መሆኑ ተገለፀ።
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ከአስር አመት ስትራቴጂካዊ እቅድ የተወሰደው የቀጣይ ሶስት ዓመታት የመካከለኛው ዘመን እቅድ (Pharmaceutical Supply Development and Investment Plan _ PSDIP) ሰነድ ክለሳ የአገልግሎቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች እና የቅርንጫፍ ስራ አስኪያጆች በተገኙበት ከታህሳስ 19-20/2016 ዓ.ም በአዳማ ከተማ አውደ ጥናት አካሄደ ።
የፈጣን ጊዜ ምላሽ አስተዳደር (Emergency supply chain managment) የህክምና መሳሪዎች አስተዳደርን ጨምሮ የመድኃኒት የመገኘት ምጣኔን በማካተት በስትራቴጂክ ግቦች እና ምዕራፎች የነባራዊ ሁኔታዎች ትንተና በጥንካሬ፣ ድክመት፣ ስጋትና መልካም አጋጣዊዎች በእቅድ ክትትል፣ ዝግጅት እና ግምገማ ዳይሬክቶሬት እየተመራ ለዚህ ስራ በተዋቀረው ኮሚቴ ተለይተው ለውይይት የቀረቡ ሲሆን ከተሳታፊዎች ለእቅዱ ግብአትነት የሚሆኑ ጠቃሚ ሀሳቦች ቀርበዋል።
ያለፈው ሶስት ዓመታትን አስመልክቶ እንደ ተቋም የቀረበውን ሪፖርት ትክክለኝነት፣ የሰነድ ክለሳ ማድረግ አስፈላጊነት ፤ ከታቀደው እቅድ ምን ያህሉ እንደተሳካ ፣ የመካከለኛ ዘመን እቅድ አሁን ላይ ያለው አፈፃፀም በውይይቱ የተነሡ ሀሳቦች ነበሩ።
አገልግሎቱ የደንበኞቹን እና ባለድርሻ አካላቱን እርካታ በማሳደግ በተለይም የመድኃኒት የመገኘት አቅምን መጨመር፣ የአቅርቦት ጥራት በማረጋገጥ፣ የፋይናንስ ወጪን መቀነስ፣ የሀብት አጠቃቀምን በማዘመን፣ የአቅርቦት ሰንሠለት መሰረተ ልማትን በመሟላት አቀርባለሁ “I_supply” ፕሮጀክት ትግበራን በቀጣይ ሶስት ዓመታት እቅድ ውስጥ በልዩ ትኩረት ለእቅዱ ተግባዊነት ማካተት እንደሚገባ የተጠቆመ ሲሆን የባለፉት ሶስት አመታት የአስር አመቱ መሪ እቅድ ሲተገበር የገጠሙ ሀገራዊ እና አለማቀፋዊ አብይ ተግዳሮቶችን እንዲሁም እነሡን ለመፍታት የተሄዱባቸውን ርቀቶች የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ሰለሞን ንጉሴ ገልጸዋል፡፡
መፍትሄ የተሰጣቸው በርካታ ጉዳዮች ቢኖሩም ለቀጣይ ሶስት ዓመታት እንደ ችግር ሆነው የሚያጋጥሙ እና በጋራ መፍታት ያሉብን እጥረቶች ላይ ይበልጥ ትኩረት አድርገን በመስራት የአቅርቦት ሰንሰለቱን ፈጣን ምላሽ ሰጭ እና የህክምና ግብአቾችን ከመቸውም በተሻለ ተደራሽ ማድረግ ይገባናል ሲሉ ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለዋል ።
# ማገልገል ክብር ነው !!
ማኅሌት አበራ
