#የአገልግሎት ጥራት አለማቀፍ የምስክር ወረቀት ለማግኘት በውጭ ኦዲተሮች የተገኙ ግኝቶች ለውይይት ቀረቡ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የተቋቋመበትን አላማ የሚሰጠውን አገልግሎት በጥረት ለመፈፀም አለም አቀፍ የምስክር ወረቀት #ISO 9001፡ 2015 ለማግኘት እና አለም አቀፍ እውቅና ያለው ተቋም ለመሆን እየሰራ ያለውን ስራ DQS በተባለ የጀርመን ሀገር መዛኝ ድርጅት በውጭ ኦዲተሮች የተገኙ ግኝቶች ለኤጀንሲው ማኔጅመንት በእምቢልታ ሆቴል ጥቀምት 10 ቀን 2014 ለውይይት ቀርቧል፡፡በተደረገው ውይይት ላይ የኤጀንሰው ዋና ዳይሬክተር የጥራት የምስክር ወረቀቱን ለማግኘት አዳማ፣ ሀዋሳ እና ዋናው መ/ቤት በተቀናጀ መልኩ እየሰሩ እንደነበር እና የጥራት ቡድኑ ግኝቶች መነሻ ሆኖ ቀጣይነት ባለው መልኩ እንደሚሰራ የእያንዳንዱ የስራ ክፍል ሚና ከፍተኛ ነው ብለዋል፡፡የምዘና ሂደቱ በደረጃ ሁለት ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የተገለፀ ሲሆን በየስራ ክፍሉ ያሉ ስራዎች በጥንካሬ ወይም በእጥረት አልተገለፁም ማለት ጥንካሬዎች ወይም ደካማ ጎኖች የሉም ማለት እንዳልሆነ ተነግሯል፡፡አራት የምዘና ቡድን አባላት ከመስረም 19 እስከ 30/2014 ዓ.ም ድረስ በዋናው መ/ቤት አዳማ እና ሀዋሳ ቅርንጫፎች ኦዲት ተደርገዋል፡፡ለኤጀንሲው ከፍተኛ አመራሮች፣ ዳይሬክተሮች፣ ስራ አስኪያጆች፣ ሰራተኞች እና GHSC-PSM Ethiopia ለነበራቸው ቀና ትብብር ምስጋና ቀርቦላቸዋል፡፡ISO 9001፡ 2015 QMS ስታንዳርዶች ደንበኞችን ፖሊሲ የስራ ሂደት ማንዋሎች መመሪያዎች እና ቁልፍ የስራ መለኪያዎችን /KPI/ ከኤጀንሲው ተግባር እና ሀላፊነት ጋር ተያይዞ ሰነዶችን በመስፈርትና በሰው ግምት ውስጥ ያስገባ ምዘና እንደነበር ተገልጿል፡፡የምዘና ሂደቱ ሲከናወን የሠነዶችን በማየት ከፍተኛ አመራሩን ቀርቦ በመጠየቅ በማድረግ የመስክ ጉብኝት የስራ ቅንጅቶችን የተሰጡ ግበረ መልሶችን በመለካት የተደረገ የአሰራር ኦዲት እንደነበር የጥራት ቡድኑ አባላት ገልፀዋል፡፡ኤጀንሲው ካሉት መልካም አጋጣሚዎች እና ጥንካሬዎች በመነሳት አለማቀፍ የጥራት የምስክር ወረቀት እንዲያገኝ የጥራት ቡድኑ የውሳኔ ሀሳብ በማቅረብ እንኳን ደሰ አላቸሀ ብለዋል። ከአሁን በፊት የኤጀንሲው ጎንደር ቅርንጫፍ የ ISO 9001፡ 2015 የጥራት የምስክር ወረቀት ማግኘቱ ይታወሳል፡፡
አወል ሀሰን
105Henok Yheyis, Tariku Zeru and 103 others7 Comments9 SharesLikeCommentShare