የኢትዮጲያ መድኃኒት አቀራቢ ኤጀንሲ ጎንደር ቅርንጫፍ ዘመናዊ አሰራርን ተከትሎ መስራት በመቻሉ ለሌሎች ተቋማት ተሞክሮ የሚቀመርበት ተቋም ሊሆን ይገባል ተባለ።

የጎንደር ቅርንጫፍ በአመቱ በአሳየዉ ከፈተኛ አፈፃፀም እንዲሁም በኢንተረናሽናል መመዘኛ የላቀ ዉጤት ማምጣቱን እና የ ISO 9001:2015 ሰርተፊከት ማግኝቱን ተከትሎ የጤና ሚንስትር የተከበሩ ዶክተር ሊያ ታደሰ ፣ የኢትዮጲያ መድኃኒት አቀራቢ ኤጀንሲ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብድልቃድር ገልገሎ ፣ የአማረ ክልል ጤና ቢሮ ከፋተኛ ሀላፊዎች ፣ የኢትዬጲያ ህብረተሰብ ጤና ኤንስቲቲዩት እና አጋር አካላት እንዲሁም የተለያዩ ሚዲያዎች ኤጀንሲዉ ያለበትን ሁኔታ የጎበኙ ሲሆን በጉብኝታቸዉ ወቅትም የኤጀንሲዉ ስራ አስኪያጅ አቶ እንዳለዉ አስማማዉ እንግዶቹን በመቀበል ጉብኝቱን የመሩ እንዲሁም ገለፃ ያደረጉ ሲሆን ሁሉም አመራሮች ኤጀንሲው እየሰራ ባለዉ ነገር መደነቃቸዉን ገልጸዋል፡፡በጉብኝቱ ላይ የተገኙት የተከበሩ የጤና ሚኒስተር ዶክተር ሊያ ታደሰ እንደተናገሩት ኤጀንሲው የጥራት ፓሊስን ከመተግበር አንፃር የሰራቸው ስራዎች ሌሎች ተቋማት ተምክሮ ሊዎስድ የሚገባው ሲሆን ተቋሙ በተለየም ጥቅምት 24 በተጀመረዉ ህግ ማስከበር ሂደት ጀምሮ መላዉ የቅርንጫፉ አመራሮች እና ሰራተኞች ግብአቶችን በግጭት ቦታ ለማደርስ እንዲሁም ተቋማትን ለመደገፈ እና ስራ ለማሰጀመር ባሳዩት ርብርብ ተቋሙ ምን ያክል ለህዝብ የቆመ መሆኑን ያሳየ ሲሆን ዛሬም በተቋሙ ተገኝተን ባየናቸዉ ነገሮች እና ተቋሙ ባስመዘገበዉ ዉጤት ተደንቀናል ከተቋሙም ብዙ መማር ያለብን ነገር እንዳለ ተመልከተናል ያሉ ሲሆን በቀጣይ ይህን ስራ ለመደገፍ ሁሌም ከጎናቸሁ ነን በማለት ተናግረዋል፡፡ የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶክተር አብድልቃድር ገልገሎ በበኩላቸው የመድሃኒት አቅርቦት ድርጅት ጎንደር ቅርንጫፍ ያስመዘገበው ውጤት እንደ ኤጀንሲ የምንኮራበት ነው ያሉ ሲሆን የተቋም ተሞክሮም በሁሉም ተቋሞቻችን ወስደው መተግበር ይኖርብናል ብለዋል አክለውም ተቋሙ ያስመዘገበውን ውጤት አጠናክሮ መቀጠል እንዲቻል ሁላችንም ድጋፋችን አጠናክረን ልንቀጥል ይገባል ብለዋል።