የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት በ10ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ዉድድር የዋንጫ ተሸላሚ ሆነ
፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨፨
አገልግሎቱ በ10ኛው ዙር ሀገር አቀፍ የጥራት ሽልማት ዉድድር ለሁለተኛ ጊዜ ተሣትፎ የ3ተኛ ደረጃ የዋንጫ ተሸላሚ ሲሆን ሽልማቱን የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልገሎ ህዳር 15 ቀን 2016 ዓ.ም. በታላቁ ቤተ-መንግስት ተቀብለዋል።
ሽልማቱ ተቋማዊ የለውጥ ስራዎች ፍሬያማ ውጤት ማስመዝገብ መቻላቸውን ማረጋገጫ ሲሆን የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልግሎት ምንም እንኳ ዘርፈ ብዙ እምርታዊ የለውጥ ጉዞ ላይ ያለ ቢሆንም ሊደርስ ሲገባው ያልደረሰባቸው ጤና ተቋማት፣ ማቅረብ ሲኖርበት ያላቀረባቸው ግብዓቶች እንዲሁም መድፈን የሚገባን ብዙ ቀዳዳዎች መኖራቸውን በውል የምንገነዘብ ሲሆን በተለያዩ መድረኮች እየተገኙ ያሉ እውቅናዎች ማህበረሰባችንን በትጋትና በቁርጠኝነት ለማገልገል የሚያበረታቱ እንጂ ከተያያዝነው ሀገራዊ ለውጥ የሚያሰናክለን አይደለም ሲሉ ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡
አክለውም በዚህ ሂደት ውስጥ ያለሰለስ ጥረት ላደረጋችሁ የአገልግሎቱ አመራሮች እና ሰራተኞች፣ የባለድርሻ አካላት ከሁሉ በላይ የተያያዝነው ለውጥ የኣቅርቦት ስርዓቱ የሚያበረክተውን ትሩፋት በመንገንዘብ ለተረዳችሁን እና ላገዛችሁን ቁልፍ ደንበኞቻችን የጤና ተቋማት ሚናችሁ ጉልህ ነበር ብለዋል።
ተቋሙ በዘንድሮው ውድድር ከዋናው መ/ቤት በተጨማሪ አዳማ ፣ ጎንደር ፣ አርባምንጭ እና ሀዋሳ ቅርንጫፎች እንዲሳተፉ በማድረግ ቅርንጫፎች በተለያየ ደረጃ የሰርተፊኬት ተሸላሚ ሆነዋል።
በቀጣይ ያሉብንን ውስንነቶች በመሙላት ተቋማዊ አሠራሮች በሙሉ መስፈርቶችን ያሟሉ እንዲሁም ተገልጋዮችን ያረኩ አንዲሆኑ የአገልግሎት ጥራት ዋንኛው የትኩረት አቅጣጫ በመሆኑ ሁሉም ቅርንጫፎች በዚህ የጥራት ሽልማት ውድድር እንዲሳተፉ በማድረግ የተጀመረው የለውጥ ስራ በማይቀለበስ ደረጃ ለይ ለማድረስ ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ዳይሬክተሩ አክለዉ ገልፀዋል።
ማገልገል ክብር ነው!
