የኤጀንሲው ሴቶች ፎረም ለተከሰተው የኮሮና ወረርሽኝ 30 ሺ ብር እና የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አደረገ፡፡

========================================
በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ የተቋቋመው የሴቶች ፎረም የኮሮና ቫይረስ በሽታን ለመከላከል እየተደረገ ያለውን ሀገራዊ እንቅስቃሴ ለመደገፍ ለአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር 30 ሺ ብር የገንዘብ ድጋፍ እና ለአትዮጵያ ካንሰር አሶሴሽን የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ ማድረጉን የኤጀንሲው የሴቶችና ወጣቶች ዳይሬክተር ወ/ሮ አለምጸሀይ ዳታ መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም ገለጹ፡፡
በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ድጋፍ ለመሰብሰብ በተዘጋጀው የባንክ አካውንት በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በኩል መጋቢት 24 ቀን 2012 ዓ.ም 30 ሺ ብር ገቢ መደጉን ዳይሬክተሯ ተናግረዋል፡፡
በተመሳሳይ ለአትዮጵያ ካንሰር አሶሼሽን 5 ሺ ብር የሚገመቱ የተለያዩ የንጽህና መጠበቂያ ቁሳቁሶች እንደ ሳሙና፣ በረኪና እና ሶፍት የመሳሰሉ ድጋፎች መደረጋቸውን ወ/ሮ አለምጸሀይ አስታውቀዋል፡፡