የኤጀንሲው የስነ-ምግባር መመሪያ በይፋ ተመረቀ ———————————————–

የኤጀንሲው የስነምግባር መመሪያ ጥር 30 ቀን 2013 ዓ.ም. በይፋ መመረቁን ስነምግባር መከታተያ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሙሉሠው አያልነህ የካቲት 01 ቀን 2013 ዓ.ም. አስታወቁ፡፡የመመሪያው አስፈላጊነት ሕግንና ስርዓትን ለማስከበር፣ የሠራተኛን መብትና ግዴታን ለማስጠበቅ፣ መልካም አፈፃፀም ያላቸው ሠራተኞችን ለመለየትና መልካም ስነምግባርን ለማበረታታት እንደሆነ ዳይሬክተሩ ገልፀዋል፡፡
በኤጀንሲው አንዳንድ የስነምግባር እንደራስ ንብረት አለማየት፣ የሃብትና ንብረት አጠቃቀም ብክነቶችና የስራ ሠዓትን አለማክበር እንደሚታዩና በቀጣይ በመመሪያው መሠረት የሕግ ተፈፃሚነት እንደሚኖራቸው አስረድተዋል፡፡ዳይሬክተሩ የመመሪያው ተፈፃሚነት በስነምግባር የታነፀ ሠራተኛን ለመቅረፅ፣ ሠራተኞችን ለማበረታታት፣ የስራ አፈፃፀም ላይ አድልዎ እንዳይኖርና ተጠያቂነትን እንዲኖር ይረዳል ብለዋል፡፡
በቀጣይም ለዋናው እና ቅርንጫፍ መ/ቤት ሠራተኞች በመመሪያው ዙሪያ ስልጠና በመስጠት የስነ ምግባር መመሪያውን ተግባራዊ እንደሚደረግና ሠራተኛውም የቃልኪዳን ስምምነት ከኤጀንሲው ጋር ፈፅሞ ግዴታውን እንደሚወጣ ዳይሬክተሩ እምነታቸውን ገልፀዋል፡፡
ከፖሜላ ስቲል አሶሴት ጋር በመተባበር ባሣለፍነው ዓመት ቢዘጋጅም ከኮቪድ 19 ጋር በተያያዘ በይፋ ወደ ትግበራ መገባት አለመቻሉን አቶ ሙሉሠው ተናግረዋል፡፡
በፀሎት የማነ