የኬሚስትሪ መመርመሪያ ሪኤጀንቶች በመሰራጨት ላይ መሆኑ ተገለጸ

ኤጀንሲው በሀገር አቀፍ ደረጃ በፕሌስመንት ግዥ ያስገባቸው የDimension Exl200 እና Cobas C311 ሪኤጀንቶችን በማሰራጨት ላይ እንደሆነ የላብራቶሪ ግብዓቶች አስተዳደር ባለሞያ ወ/ሮ ሚዛን ገ/ዮሐንስ አስታወቁ፡፡
ሪኤጀንቶቹ የኬሚስትሪ መመርመሪያ ሲሆኑ ከዚህ ቀደም የሕክምና መሣሪያዎቹ ለተተከሉባቸውም አዲስ ተከላም ለተካሄደላቸው የጤና ተቋማት እየተሰራጩ መሆኑ ተገልጿል፡፡
ሪኤጀንቱ በሁሉም ከቅርንጫፎች አማካኝነት የሚሠራጭ ሲሆን ከዚህ ቀደም የነበረውን የላብራቶሪ ቴስት መቆራረጥ ቅሬታ በመፍታት ለህብረተሰቡ የተሟላ የላብራቶሪ አገልግሎት ለመስጠት ያስችላል፡፡ሪኤጀንቶቹ 117 ሚሊዮን 680 ሺህ 794 ብር ወጪ እንደተደረገባቸው በቃለ መጠይቁ ያገኘነው መረጃ ያሣያል።
ሂሩት ኃይሉ