የክትባት አስተዳደርን ለማጠናከር እና የባለድርሻ አካላትን ቅንጅት ለማምጣት ያለመ ወርክሾፕ በአዳማ ከተማ ካኖፒ ሆቴል ተካሄደ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ አገልገግሎት ለጤና ተቋማት የሚያቀርባቸውን መደበኛም ሆነ የኮሮና ክትባቶች የተቀመጠላቸውን የሙቀት እና ቅዝቃዜ ስታንዳርድ ተጠብቆላቸው ወደ ሀገር ውስጥ ሲገቡ ፈዋሽነታቸውን ጠብቀው መሆን እንዳለት ለዚህም የቁልፍ ባለድርሻ አካላት ሚና ከፍተኛ መሆኑን አቶ ሰለሞን ንጉሴ የአገልግሎቱ ም/ ዋና ዳይሬክተር መጋቢት 17 ቀን 2014 ዓ.ም ተናግረዋል፡፡ከቁልፍ ባለ ድርሻ አካላት ጋር የተደረገው ምክክር በዋነኛነት በክትባቶች አስተዳደር ሂደት የሚገጥሙ፣ እየገጠሙ የሚታዩ ችግሮችን በመለየት ፣ለችግሮቹ የጋራ መፍትሄ የሚሆን የድርጊት መርሃ ግብር በመውሰድ፣ የሚነሱ ዋና ዋና የአሰራር ችግሮችን ለመወያየት እና ለመፍታት ለክትባት አቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር አጋዥ እርምጃዎችን ለመንደፍ መሆንኑ ተገልጻል፡፡ አሁን እየታየ ካለው ያልተመጣጠነ የመድሃኒት አቅርቦት እና ፍላጎት ወደ ተመጣጠነ የመድሃኒት አቅርቦት እንዲኖር በፍጥነት ለመጓዝ ከባለድርሻ አካላት ህብረት፣ቅንጅት እና ትብብር ከመቼውም በላይ አስፈልጎናል ያሉት ምክትል ዋና ዳይሬክተሩ “የአቅርቦት ሰንሰለት ትልቅ ጠላት ቢኖረው ከባለድርሻ አካላት ጋር ያለ የመልካም ግንኙነት ወይም የተግባቦት መጓደል ነው ” ብለዋል። ባለድርሻ አካላት መደማመጥ እስከቻልን ድረስ ለስኬታችን ትልቅ አስተዋጽኦ በማመርከት ለችግሮቻችንም መፍቻ ቁልፍ ናቸው ስሉ አቶ ሰለሞን ተናግረዋል፡፡በጣም የተጋነነ እስከ 300% የሚደርስ የጭነት እና ማከማቻ ዋጋ ለትራንስፖርት እየከፈልን ነው፣ከውጭ የምናስመጣናቸውን የህክምና ግብአቶች በአጭር እና በተቀናጀ ከትርንስፖርት ተቋማት ማስለቀቅ/clear /ማድርግ ፈተና መሆኑን እንዲሁም ከፈረንጆቹ ሚያዚያ 2018 ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ለመደበኛ እና የኮረኛ ክትባቶች ከጉምሩክ እና ከቁጥጥር ባለስልጣን ጋር ለተያያዙ ቀረጦች ክስከ 90 ሚሊዮን ብር እንድናወጣ ሆኖል በማለት የተናገሩት የአገልግሎት ተቋሙ የኮንትራት አስተዳደር ዳይሬክተሩ አቶ ናሆም ገመቹ ካለን መድሃኒትን ለህብረተሰቡ በተመጣጠኝ ዋጋ ከማድረስ ሀገራዊ ተልእኮ አኳያ መዘግየት ሳይኖር ቅድሚያ የመስተናገድ እድል ከባለድርሻ አካላት ሊሰጠን ይገባል ብለዋል።ከእያነዳንዱ ባለድርሻ አካል የሚስተዋሉ ችግሮች የተለዩ ሲሆን ለውይይት የሚሆኑ ሀሳቦች ቀርበው የጋር ምክክር ከተደረገባቸው በኃላ በተፈጠረው ግንዛቤ ሁሉም የየድርሻውን በመውሰድ የትግበራ የድርጊት መርሀ ግብር ወጥቷል፡፡የኢትዮጵያ መድሀኒት አቅራቢ አገልገግሎት ከብሄራዊ ባንክ/ NBE/፡ከንግድ ባንክ/ CBE/፡ከ ኢንሹራንስ ድርጅቶች፡ከጉምሩክ ኮሚሽን፡ከምግብ እና መድሃኒት ቁጥጥር ባለስልጣን/ EFDA/ ከባህር ትራንስፖርት እና ሎጀስቲክስ/ ESLSE/ ከመንግስት ንብረት አስተዳደር እና ግዥ/ PPA/፡ከጤና ሚንስቴር/MoH/ ከኢትዮጵያ አየር መንገድ/EEL/ ከለጋሾች እና ከአጋር ድርጅቶች ጋር በህክምና ግብአቶች አቅርቦት ዙሪያ በጋራ እንደሚሰራ ታውቋል፡፡ በየኒሴፍ /UNICEF/በኩል ከጤና ሚንስቴር ጋር ባለው ስምምነት መሰረት የኮቪድ19 ክትባት፡ የቅዝቃዜ ሰንሰለት እቃዎች እና መከላከያ ግብአቶች ከ116.2 የአሜሪካ ዶላር በላይ ግዥ በማከናወን ለአገልግሎት ተቋሙ ማቅረቡ ተገልጻል፡፡
አወል ሀሰን