የኮቪድ-19 መከላከያና መቆጣጠሪያ ግብዓቶች እየተሰራጩ እንደሆነ ተገለጸ —————————————————-

April 26, 2021Uncategorized @am
ኤጀንሲው የኮቪድ-19 በሽታን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የሚያገለግሉ ግብዓቶችን እያሰራጨ መሆኑን የስርጭት ከፍተኛ ባለሞያ አቶ ነብዩ ይትባረክ አስታወቁ፡፡ኤጀንሲው በሀገራችን የኮቪድ-19 ወረርሽኝ ከተከሰተበት ጊዜ አንስቶ እስካሁን በተለያዩ ዙሮች የተለያዩ መድኃኒቶችን፣ የሕክምና መርጃ መሣሪያዎችንና ግብዓቶችን ያሰራጨ ሲሆን አሁን ለ11ኛ ጊዜ ስርጭት እያካሄደ ይገኛል፡፡
ከተሰራጩት ግብዓቶች መካከል Alcohol Based Hand Sanitizer, Face Shield, Cover All, Eye Goggle, Face Mask, Soap powder, Chemical-Alcohol Denatured, ventilator-Mechanical ICU, Apron Plastic Protection against Most Chemical 80 X120cm, Bed Sheet እና Bandage Elastic መሰራጨቱን ባለሞያው ገልጸዋል፡፡ስርጭቱም በኤጀንሲው ቅርንጫፎች አማካኝነት ለሁሉም ክልሎች፣ ለአዲስ አበባ እና ለድሬደዋ ከተማ መስተዳደሮች እየተሰራጨ ሲሆን 35 ሚሊዮን 448 ሺህ 237 ብር ወጪ ተደርጎባቸዋል፡፡
ሂሩት ኃይሉ