የዩኒሴፍ የመድኃኒት አቅርቦት ዘርፍ ዳይሬክተር ኢትሌቫ ካዲሊ የተመራ የልኡካን ቡድን በኤጀንሲው ጉብኝት አካሄደ።

በኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በዩኒሴፍ የመድኃኒት አቅርቦት ዘርፍ ዳይሬክተር ኢትሌቫ ካሊዲ የተመራ የልኡካን ቡድን መስከረም 13 ቀን 2014 ዓ.ም ጉብኝት አካሄዷል።በጉብኝታቸው ወቅት ኤጀንሲው በአቅርቦት ሰንሰለቱ ትኩረት ሰጥቶ በመስራት ለማህበረሰቡ መሰረታዊ የህይወት አድን መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ተደራሽ ለማድረግ በአጭርና በረጅም ጊዜ ሊሰራቸው ያሰባቸውን እቅዶች ዳይሬክተሯ አድንቀዋል።እንዲሁም እቅዱን እውን ለማድረግና የአቅርቦት ሰንሰለቱን ለማዘመን በአቅም ግንባታና በተለያዩ ዘርፎች ድጋፋቸውን አጠናክረው እነደሚቀጥሉ ቃል ገብተዋል።ኤጀንሲው ከዩኒሴፍ ጋር ላለፉት አስራራት አመታት በክትባት መድኃኒት አቅርቦት፣ በአቅም ግንባታና በሌሎች ተያያዥ ጉዳዮች ላይ በጋራ መሰራቱን የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልጋሎ ተናግረዋል።የጉብኝቱ ዓላማ ኤጀንሲው በቀጣይ አስር ዓመት ትልቅና ዘመናዊ የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘን ለመገንባት ያቀደ በመሆኑ ከዲዛይን እስከ ግንባታው መጠናቀቅ ድረስ በልምድ ማጋራትና በአቅም ግንባታ በጋራ ለመስራት እንደሆነ የኤጀንሲው ም/ክ ዋና ዳይሬክተር አቶ ተስፋለም አድራሮ አብራርተዋል።ም/ዋና ዳይሬክተሩ አክለውም ለድንገተኛ አደጋ ፈጣን ምላሽ በመስጠት በኩል የዩኒሴፍን ልምድና ተሞክሮ ለመጋራት ጉብኝቱ ከፍተኛ ሚና እንደሚኖረው ተናግረዋል።በአሁኑ ወቅትም ከክትባት መድኃኒት አቅርቦቱ ባሻገር በተለያዩ ምክንያቶች በምግብ እጥረት ለተጎዱ የህብረተሰብ ክፍል እየተደረገ ላለው የአልሚ ምግቦች ድጋፎም ምስጋና አቅርበዋል::ኤጀንሲው በቀጣይ አስር ዓመት እቅዱ ሊያከናውናቸው የያዛቸውን እቅዶች ከግብ ለማድረስ አጋርነታቸው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ዋና ዳይሬክተሩ እምነታቸውን ገልጸዋል፡፡ዩኒሴፍ ከኤጀንሲው ጎን በመሆን ላበረከታቸው ዘርፈ ብዙ ስራዎች ለልኡካን ቡድኑ የምስጋና ስጦታ ተበርክቷል።በጉብኝቱ መረሃ ግብር የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር፣ ከፍተኛ አመራሮችና ዳይሬክተሮች ተገኝተዋል።