የደሴ ቅርንጫፍ 2ተኛ ደረጃ በወውጣት ከኤጀንሲው እውቅና አገኝ፡፡

በኢትዮጵያ መድሃኒት አቅራቢ እጀንሲ አመታዊ ዕቅድ ክንውን ምክክር በጎንደር ከተማ ባደረገበት ወቅት የኤጀንሲው የደሴ ቅርንጫፍ በልህቀት ማእከል ትግበራ እንድሁም በአመታዊ ህክምና ግባዓቶች ቆጠራ ክንውን 80 %በማግኘት የ 2ተኛ ደረጃን እውቅና አግኝቶል፡፡
የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ የሆኑት አቶ እሸቴ ሹሜ እንደገለጹልን ይህ እውቅና የተገኘው ማኔጅመንቱ ፡የትግበራ ቡድኑ/task force/በጣም ትጉህ የሆን ሰራተኞች እንችላለን ብለን አዳማ ላይ የተሰጠንን ኦሬንቴሽን ስለተገበርን ነው ብለዋል፡፡
ከባለፈው ሰኔ 1 የቆጠራ ስራ/inventory/ጀምረን ሀምሌ መጨረሻ ስናጠናቅቅ አምሽተንምጭምር በመስራት ሰራተኞች አቧራ ሲያጸዱ ፓሌት እያጠቡ ላበረከቱት ገንቢ አስተዋጽኦ አውቅናውይገባቸዋል ሲሉተናግረዋል፡፡
ከዋናው መ/ቤት ፡ከአዳማ ቅርንጫፍ እንድሁም ከግሎባል ሄልዝ የነበረው ድጋፍ የተሻልን እንድንሆን ረድቶናል ያሉት አቶ እሸቴ የዛሬው ውጤት የነገው ስላልሆነ የበለጠ ጠንክረው መስራት እንዳለባቸው ገልጸዋል፡፡
በተጨማሪም በ2ዐ11 ዓ.ም በጀት ዓመት ደሴ ቅርንጫፍ የ160,416,662 ብር የመደበኛ መድሃኒት (RDF) እና የፕሮግራም 733,333,337 ብር የስርጭት ዕቅድ ተይዞ የነበር ሲሆን አፈጻጸሙም የመደበኛ መድሃኒት 230,183,902.54 ብር ሲሆን የፕሮግራም ደግሞ 687,972,261.06 ብር ነው ብለዋል፡፡
ይህም በዕቅድ ተይዞ ከነበረው ጋር ሲነጻጸር የመደበኛ143.5%የፕሮግራም 93.8%በድምሩ 102.7% እንደሆነ ከ ስራ አስኪያጁ ማብራሪያ ተረድተናል ፡፡
በቀጥታ
በየ2 ወሩ የሚደርስላቸው ጤና ተቋማት ወረዳን ጨምሮ ብዛት 257 ሲሆኑ
ለ 60 ወረዳዎችØ
ለ 26 ሆስፒታሎችØ
ለ 110 ART Site አገልግሎት ለሚሰጡ ጤና ጣቢያዎችØ
ከ 157 PMTCT Site የመንገድ ተደራሽ ላላቸው 60 ጤና ጣቢያዎችØ
ለ 1 ሪጅናል ላቦራቶሪ ደሴ/ እና በወረዳ በኩል የሚደርስላቸው ለ154 ART Site ላልሆኑ ጤና ተቋማትØ
o አፋር ክልል በ 2 ወረዳዎች ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት
አማራ ክልል በ 58 ወረዳዎች ስር ለሚገኙ ጤና ተቋማት አገልግሎት የሚውሉ የኘሮግራም መድኃኒቶች፣ የህክምና መገልገያዎችና የህክምና መሳሪያዎች ለማሰራጨት የቻለ ቅርንጫፍ መሆኑን አቶ እሸቴ ገልጸዋል ፡፡
እኛም
የደሴ ቅርንጫፍን እንኳን ደስ አላችሁ እንላለን!!!
Supply chain of compassion!!!!!!