የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ ከኤጀንሲው ማኔጅመንት ጋር ውይይት አካሄዱ ————————

የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ደረጀ ዱጉማ የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ በአስር ዓመት የመድኃኒት አቅርቦት ትራስፎርማሽን እቅድ እና በ2013 በጀት ዓመት እቅድ ላይ ከማኔጅመንት አባላት ጋር ማክሰኞ ሐምሌ 14 ቀን 2012 ዓ.ም ውይይት አካሄዱ፡፡
ዶ/ር ደረጀ እና የሥራ ባልደረቦቻቸው የኤጀንሲውን የመድኃኒት ማከማቻ መጋዘኖችና የተለያዩ ቢሮዎችን ተዘዋውረው ከተመለከቱ በኋላ የኤጀንሲው የአስር ዓመት የመድኃኒት አቅርቦት ትራስፎርሜሽን እቅድ እና የ2013 በጀት ዓመት እቅድ ቀርቦ ሰፊ ውይይት አድርገዋል፡፡
በውይይቱ በቀጣይ በጀት ዓመት ጤና ሚኒስቴር ተቋሙን ትኩረት አድርጎ ሊደግፋቸው የሚገቡ ጉዳዮች የተነሱ ሲሆን በተለይም ለሠራተኛው ምቹ የሥራ አካባቢ ከመፍጠር አኳያ እና የተጀመረው G+7 ህንጻ እንዲሁም በፋይናንስ ራስን የመቻል ጉዳዮችና ሌሎች ውይይቱ ከተደረገባቸው ጉዳዮች መካከል ተጠቃሾች ናቸው፡፡
የኤጀንሲው ዋና ዳይሬክተር ዶ/ር አብዱልቃድር ገልጋሎ በበኩላቸው የተያዙትን እቅዶች ማሳካትና ያጋጠሙ ችግሮችን መፍታት የሚቻለው በዋናነት የተቋሙ አመራሮችና ሰራተኞች በመቀጠል ደግሞ የጤና ሚኒስቴር ድጋፍ መሆኑን በመገንዘብ ጠንክረን መስራት ይኖርብናል ብለዋል፡፡
ዶ/ር ደረጀ በጤናው ሴክተር የተያዙ እቅዶችን ውጤታማ ለማድረግ ግብዓት ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰው ተቋሙን በቅርበት ለመደገፍ እና በጋራ ለመሥራት ቁርጠኛ መሆናቸውን በማጠቃለያ ውይይታቸው ገልጸዋል፡፡