የጥራት ፖሊሲ

የኢትዮጵያ መድኃኒት አቅራቢ ኤጀንሲ(ኢመአኤ) ጥራታቸው የተረጋገጠ መሠረታዊ መድኃኒቶችን በተመጣጣኝ ዋጋ ለመንግሥት የጤና ተቋማት በዘላቂነት ለማቅረብ በትጋት ይሰራል፤ይህንንም ለማሳካት የሚከተሉትን ስትራቴጂክ ግቦች ተግባራዊ ያደረጋል፡፡
- በፋይናንስ እና በአሰራር ስርአት ራስን መቻል፤
- ከላቀ የደንበኞች አገልግሎት ጋር መድሃኒቶችን በበቂ ሁኔታ እንዲገኙ ማድረግ፤
- የአቅርቦት ሰንሰለት አስተዳደር የሰው ሀይል አቅም እና ሙያዊ እርካታ ማሳደግ፤
- ከጊዜው ጋር የሚሄድ የአሰራር ባህል በመፍጠር እና ዓለምአቀፋዊ ደረጃን በጠበቀ መልኩ ኤጀንሲው አዳዲስ የሥራ አጋጣሚዎችን እንዲጠቀም ማስቻል፡፡
የእለት ተእለት እንቅስቃሴያችን ከፍተኛ የሥነምግባርና የሙያተኝነት ደረጃን በማሳየት እሴቶቻችንን ያንፀባርቃል፤እንዲሁም ብቃትንና ፈጠራን በአቅርቦት ሰንሰለቱ ውስጥ ያበረታታል፡፡
የኤጀንሲው ከፍተኛ አመራር ሕጎችና ደንቦችን አክብሮ እና የጥራት አስተዳደር ስርዓትን በቀጣይነት አሻሽሎ የደንበኞችንና የባለድርሻ አካላትን ፍላጎት ለማርካት እንዲሁም የተቋሙን ተልዕኮ በዘላቂነት ለማሳካት ቁርጠኛ ነው፡፡